የኢትዮጵያ አየር መንገድ “አውሮፕላን ከአምራቾች በሚፈለገው ልክ እየቀረበ ባለመሆኑ በኪራይ እስከመሥራት ደርሻለሁ” አለ

አውሮፕላን ከአምራቾች በሚፈለገው ልክ እየቀረበ ባለመሆኑ ተከራይቶ እስከመሥራት ደርሻለሁ ሲል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ገለጸ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በኢፕድ ከምትዘጋጀው ዘመን ኢኮኖሚ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ አውሮፕላን አምራቾች በሚፈለገው ልክ እያመረቱ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ እያቀረቡ ዓይደለም።
በዚህ ምክንያት አየር መንገዱ ከገበያ ላይ ኪራይ እያፈላለገ እስከመሥራት መድረሱን አስታውቀዋል፡፡
ከአውሮፕላን ምርት አቅርቦት እጥረት ባሻገር የአውሮፕላን ዕቃ የመለዋወጫ እጥረት መኖሩንም አመላክተዋል።
አየር መንገዱ አሁን ላይ ከ149 በላይ አውሮፕላኖች እና ከ135 በላይ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች አሉት፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe