እስራኤል ትላንት በሃማስ የተሰጣት አስክሬን የጋዛ ታጋች አለመሆኑን አረጋግጫለሁ አለች፡፡
የእስራኤል የፎረንሲክ አገልግሎት ቡድኑ ትላንት ማክሰኞ ያስረከባቸው ቀሪ ሁለት አስክሬኖች ከቀሩት ውስጥ የነበሩት አለመሆኑ ተረጋግጧል ብሏል፡፡
ቡድኑ ትላንት በኦክቶበር 10 በተደረሰው የሰላም ስምምነት መሠረት የመጨረሻዎቹን ሁለት የእራኤል ታጋች አስክሬኖችን ለቀይ መስቀል ማስረከቡን ገልጾ ነበር፡፡
ምንም እንኳን ሃማስ በጋዛ የቀሩ የእስረኤል ታጋች አስክሬኖችን ትላንት ማስረከቡን ቢገልጽም ነገርየው ውዝግብ ቀስቅሷል፡፡
ቡድኑ የቀሩ ታጋቾች አስክሬን ነው በሚል ትላንት ለእስራኤል ቢያስረክብም እስራኤል ግን የተመለሱት የቀሩት ታጋች አስክሬን አይደሉም ብላለች፡፡
እስራኤል ሃማስ ሆን ብሎ እንዳረገው እንደምታምን ገልጻ፤በሁኔታው መቆጣቷንም ገልጻለች፡፡
የታጋች ቤሰቦች መልካም ዜና እየጠበቁ ባለበት ስዓት የደረሰን የታጋች አስክሬን ሌላ ነው ብላለች፡፡ ሀማስ እንዲህ አይነት ሀሰተኛ መረጃዎችን የሚሰጥ ከሆነ ድርድሩን ውስብስብ ሊያደርገው እንደሚችል አስታወቃለች፡፡
ምን አልባነት ቡድኑ ይህንን ያደረገው የልየታው ስራ ከአቅሙ በላይ ሆኖበት በስህተት ወይንም አሁንም አቅም እንዳለው ለማሳየት አድርጎት ሊሆን እንደሚችል ይታመናል፡፡//

