የእንጀራን ዓለም አቀፍ ሽያጭ ለማሳደግ የጥራት ደረጃ እየተዘጋጀለት እንደሆነ ተገለጻ

እንጀራን በመላው ዓለም ለማስተዋወቅ የሚረዳ ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃ እየተዘጋጀ እንደሆነ ተሰማ፡፡ ይህ የጥራት ደረጃ በውጪ ካሉ ኢትዮጽያዊያን በተጨማሪ የሌላ ሀገር ዜጎች እንጀራን እንዲመገቡ የማድረግ ሚና ይኖረዋል ተብሏል፡፡

በዚህ ወቅት ከእንጀራ የወጪ ንግድ የሚገኘው ገቢ ጥሩ ደረጃ ላይ ቢሆንም፤ገቢው የጨመረው የኢትዮጽያዊያንና ትውልደ ኢትዮጽያዊያን እንጀራ ተመጋቢዎች ቁጥር ከፍ በማለቱ እንጂ የሌላ ሀገራት ዜጎች እንጀራ የመመገብ ፍላጎት ስላደገ አይደለም ተብሏል፡፡

በዚህ መሰረትም እንጀራን ለመላው ዓለም ተመጋቢዎች በበቂ መጠን ማስተዋወቅ እንደሚያስፈልግ የእንጀራ ጋጋሪ እና ላኪዎች ማህበር አስታውቋል፡፡

ማህበሩ በዚህ ስዓት በብዛት እንጀራን የሚልከው ወደ ሰሜን አሜሪካ ሀገራት መሆኑንም ገልጻል፡፡

ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የሌሎች ሀገራት ዜጎችም እንጀራን እንዲመገቡ የማስተዋወቅ ስራ ያስፈልጋል ብሏል፡፡

የኢትዮጽያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት የእንጀራን ዓለም አቀፍ ሽያጭ ለማሳደግ የደረጃ እየተዘጋጀለት እንደሆነ ገልጻል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe