በሚያዝያ 19/ 1917 ዓ.ም ተመርቆ የተከፈተውና በኢትዮጵያ የዘመናዊ ትምህርት ሥልጠና ታሪክ ቀደምት ሥፍራ ካላቸው ተቋማት ውስጥ የሚመደበው የተፈሪ መኮንን ትምህርት ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ ስሙ ወደ እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተቀይሮ ሲጠራበት ቆይቷል።
እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በመስራቹና በቀድሞ ስያሜው አልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን ስም ድጋሚ እንዲሰይም የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ሲደረጉ እንደነበር ተነግሯል።
“እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ”ስያሜ የተቋሙን ታሪክና ቦታ የማይወክል በመሆኑና ዘንድሮ የሚከበረውን የትምህርት ቤቱን መቶኛ ዓመት አስመልክቶ ስያሜውን በዚህ ሳምንት ወደ “ተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ” ተብሎ እንዲመለስ እንደተደረገ አርትስ ስፔሻል ከተቋሙ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ትምህርት ቤቱ ባስቆጠረው አንድ መቶ ዓመታት በተለያዩ ዘርፎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ዜጎች በማስተማርና በማሠልጠንም፣ ኢትዮጵያ በተለያዩ ወቅቶች ለነበሯት የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የማኅበራዊ ጉዳዮች ምላሽ የሚሰጡ ባለሙያዎችንም ያፈራ ነው፡፡
Via: አርትስ ቲቪ
የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስያሜውን ወደቀድሞ “ተፈሪ መኮንን” መለሰ

