የኬንያ ገለልተኛ የፖሊስ ተቆጣጣሪ ተቋም ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ተጠርጥሮ በእስር ላይ የነበረውን ኬኒያዊ ግድያ በተመለከተ ምርመራ መክፈቱን የሀገሪቱ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በኤክስ ገጹ ላይ ባጋራው ልጥፍ ምክንያት በቁጥጥር ስር የዋለው አልበርት ኦጅዋን በምዕራባዊ የሀገሪቱ ክፍል በምትገኘው ሆማ ቤይ ከተያዘ በኃላ ወደ ናይሮቢ ተወስዶ ቆይቷል፡፡
ፖሊስ ባወጣው መግለጫ ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር እያለ ጭንቅላቱን ከእስር ቤቱ ግድግዳ ጋር በማጋጨቱ የጭንቅላት ጉዳት ደርሶበታል ብሏል፡፡
የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ተቋም አምነስቲ አኒንተርናሽናል የመምህርሩና የጦማሪው ሞት አጠራጣሪ ነው ብሎታል፡፡
አምነስቲ የግለሰቡ ሞት በአስቸኳይ እና በጥልቀት መመርመር እንደሚኖርበት ገልጻል፡፡
የኬኒያ ፖሊስ በእስር ቤት ውስጥ የተፈጠረው ራስን የማጥፋት ሙከራ እንደሆነ መግለጹ ተነግሯል፡፡/

