የኬንያ የምርጫ ኮሚሽን ለፕሬዚዳንታዊ ዕጩዎች የ34 ሚሊዮን ዶላር፣ ለፓርቲዎች ደግሞ የ136 ሚሊዮን ዶላር የቅስቀሳ ወጪ ጣሪያ ሃሳብ አቀረበ
🇰🇪 ረቂቁ በምርጫ ወቅት የገንዘብ ተፅዕኖን ለመቀነስ፣ ፍትሐዊነትን ለማስፈን እና ፓርቲዎች የገቢ ምንጫቸውን ይፋ እንዲያደርጉ ለማስገደድ ያለመ ነው።
የቀረበው ገደብ የሚከተሉትን ጨምሮ ሁሉንም የቅስቀሳ ወጪዎች ያካትታል፦
🔸 የሕዝብ ማስታወቂያ ቁሳቁሶችን፣
🔸 ማስታወቂያዎችን፣
🔸 የቅስቀሳ ሠራተኞችን እና የትራንስፖርት ወጪዎችን፣
🔸 የዕጩነት ምዝገባ ክፍያዎችን፣
🔸 አስተዳደራዊ ወጪዎችን።
እነዚህ የወጪ ገደቦች በጠቅላላው የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የሚተገበሩ ሲሆን እንደ ምርጫው ዓይነትም ልዩነት ይኖራቸዋል።

