የወርቅ ሽያጭ ከ2.57 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለጸ

በ10 ወራት የወርቅ ሽያጭ ከ2.57 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለጸ፡፡

በእነዚሁ ወራቶች ውስጥ ወርቅ አምራች ከሆኑ ከልሎች ከ29ሺ396 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ ተልኳል መባሉ ታውቋል፡፡ ትግራይ ክልል ከፍተኛ የወርቅ ምርትን ለብሔራዊ ለባንክ በመላክ ከክልሎች ቀዳሚ እንደሆነም ተሰምቷል፡፡

በዚህም መሠረት ትግራይ ክልል 12ሺ210 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ማቅረቡ ሲነገር ኦሮሚያ 6ሺ910 ኪሎ ግራም፡ጋምቤላ 4ሺ590 ኪሎ ግራም እንዲሁም ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 3ሺ689 ኪሎ ግራም ወርቅ ማቅረባቸውን የማዕድን ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል፡፡

የተገኘው የወርቅ ምርት ጨምሯል የተባለ ሲሆን ለዚህም ብሔራዊ ባንክ በባህላዊና በአነስተኛ መጠን ወርቅ ምርት ላይ ለተሰማሩ አምራቾች ተግባራዊ እንዲሆን የወሰነው ማበረታቻ መነቃቃት እንዲፈጠርና ህገ ወጥ ንግዱም እንዲቀንስ በማድረጉ ነው ተብሏል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe