የዓለማችን ‘ትልቁ’ ቤተሰብ አባወራ አረፉ

በሕንድ የበርካቶች ወላጅ አባት እንደሆኑ የሚታመኑት የ76 ዓመቱ አዛውንት አረፉ።
አዛውንቱ በሕንድ ሞሚዞራም በምትባል ግዛት ነዋሪ የነበሩ ሲሆን እሁድ እለት መሞታቸው ተገልጿል።
ዚዮና ቻና የሚባሉት እኚህ አዛውንት በርካታ ሚስቶችን ማግባት የሚፈቅድ ሐይማኖት ተከታይ የነበሩ ሲሆን፤ 38 ሚስቶችን አግብተው፣ 89 ልጆችን እንዲሁም 36 የልጅ ልጆችን አፍርተው ነበር።
የአዛውንቱ መሞት በአካባቢው አስተዳዳሪ የተረጋገጠ ሲሆን፣ ባለሥልጣኑ በትዊተር ሠሌዳቸውም ላይ በሞታቸው የተሰማቸውን ሐዘን አስፍረዋል።
አዛውንቱ የደም ግፊት እና ስኳር ሕመምተኛ እንደነበሩ ክትትል ሲያደርጉላቸው የነበሩ የሕክምና ባለሙያዎች ገልፀዋል።/bbc/

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe