የዓለም የምግብ ፕሮግራም በኢትዮጽያ ለተረጂዎች እየሰጠ ያለው የሰብአዊ እርዳታ ከቀናት በኋላ ሊቆም እንደሚችል ገለጸ

የገንዘብ ድጋፍ ባለማግኘቱ ለተረጂዎች እያከፋፈለ የሚገኘውን እርዳታ በከፍተኛ መጠን መቀነሱንም አመልክቷል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም WFP ባጋጠመው የገንዘብ ድጋፍ እጥረት በሰኔ ወር በኢትዮጽያ እያካሄደ ያለውን ድጋፍ እንደሚያቋርጥ ይፋ አድርጓል፡፡

በአሁኑ ወቅትም የሚሰጠውን የምግብ እርዳታ መጠን ቀድሞ ከነበረበት መጠን ቀንሶታል፡፡ የፈንድ እጥረት በኢትዮጽያ የምግብ እርዳታ ድጋፍ ማድረጉን ለማስቀጣል ያለውን አቅም እየገበደበው እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

ተቋሙ በዚህ ስዓት በድጋፍ መልክ እያቀረበ ያለው ምግብ በእስታንዳርዱ መሠረት አንድ ተረጂ እንዲያገኝ ከሚጠበቀው በታች 65 በመቶውን ብቻ መሆኑንም አሳውቋል፡፡ በዚህም መሠረት በአሁኑ ወቅት ለአንድ ተረጂ ቤተሰብ እያቀረበው ያለው መጠን 9 ኪሎ ግራም እህል፡አንድ ኪሎ ጥራጥሬ እና አንድ ነጥብ አንድ ኪሎ የምግብ ዘይት ብቻ መሆኑን ገልጻል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe