የዩቶፕያ ግሪን ፈንድ የኤሌክትሪክ መኪና እቁብ ለቆጣቢዎች አወጣ

የዩቶፕያ ግሪን ፈንድ ሲስተምን በመጠቀም ላለፉት 4 ወራት ለመኪና እቁብ ሲቆጥቡ ለነበሩ ደንበኞች የመኪና እቁብ እጣ አወጣጥ ስነስርአት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና ታዛቢዎች በተገኙብት ቅዳሜ በስካይ ላይት ሆቴል ተከናውኗል። ፕሮጀክቱ ኢትዮጽያ ለምትከተለው አረንጓዴ-መር ዲጂታል ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋዖ የሚያበረክት መሆኑ ተነግሯል።

የዩቶፕያ ቴክኖሎጂ ኃላ.የተ.የግ.ማኅበር መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አዶኒክ ወርቁ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር  እንደገልጹት “ድርጅታችን ላለፉት 5 አመታት ሲሰራበት የቆየውን በኢትዮጵያ ፈርቀዳጅ የሆነውን እና ለአካባቢ ንብረት ተስማሚ እንዲሁም ለነዳጅ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬንየሚያስቀር ዩቶፕያ ግሪን ሞቢሊቲ ኢኒሼቲቭ እየተገበረ ሲሆን በውስጡ “ዩቶፕያ አውቶሞቲቭ” ፣ “ዩቶፕያ ኢ፟ ታክሲ” ፣ “ዩቶፕያ ግሪን ፈንድ” እና “ዩቶፕያ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጂንግ እስቴሽን” ፕሮጀክቶች ያካተተ ሲሆን ፕሮጀክቱ ሀገራችን ለምትከተለው አረንጓዴ-መር ዲጂታል ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክት ፤ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት እንደ ኢምፖርት ሰብስቲትዩት ለመጠቀም እና የኢነርጂ ፍላጎታችንን አካባቢ በካይ ከሆነው ነዳጅ በዋጋ ዝቅተኛ ታዳሽ ኤልክትሪክ ሀይል ለመቀየር ትልቅ እድል ይፈጥራል እንዲሁም ለነዳጅ የሚወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ያስቀራል፡፡በተጨማሪም ለህብረተሰቡ ከፍተኛ የስራ እድል ከመፍጠሩ ባሻግር ያለውን ከፍተኛ የትራንስፖርት እጥረት ይቀርፋል” ብለዋል ፡፡

ዩቶፕያ ግሪን ፈንድ “(Utopia Green Fund) ኢንተግሬትድ የኤሌክትሪክ የመኪና ፍይናንሲንግ ሲስተም በ5 አመት ውስጥ 5,000 ደንበኞችን የኤሌክትሪክ የመኪና ባለቤት ለማድረግ እንዳቀደ ተነግሯል።

እስካሁንም 1,650 አባላት ሲስተም ላይ መመዝገባቸው ታውቋል።

ሙሉ ቅድመ ክፍያ መክፈል የማይችሉ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከተለመደው የመኪና ፋይናንሲንግ በተለየ አስከ 5 አመት ድረስ እየሰሩ የሚከፍሉበት የመኪና ሊዝ አከፋፈል መመቻቸቱ ተነግሯል።//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe