የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች ጆሯቸውን በፋሻ በማሸግ ድጋፋቸውን እየገለጹ ነው

 የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ለዶናልድ ትራምፕ ድጋፋቸውን ለማሳዬት ጆሯቸውን በፋሻ በማሸግ በሪፐብሊካን ፓርቲው ብሔራዊ ኮንቬንሽን ላይ እየታደሙ ነው።
በዊስኮንሲን የተሰባሰቡት የፓርቲው አባት ድርጊቱን ዶናልድ ትራምፕ ያላቸውን ድጋፍ ለማሳዬት ያለመ ነው ብለዋል።
በኮንቬንሽኑ ለመታደም ከአሪዞና ግዛት የመጡት የፓርቲው ልዑካንም በተመሳሳይ ልክ ዶናልድ ትራምፕ በተደረገባቸውን የግድያ ሙከራ አንድ ጆሯቸው ቆስሎ እንደታሸገው ሁሉ እነሱም ድጋፍና አጋርነታቸውን ለማሳዬት በፋሻ አሽገው ታይተዋል።
አንድ የሳቸው ደጋፊ ጆሮየን በፋሻ ያሰርኩት ለሳቸው ያለኝን ፍቅር መለግለፅ ነው ብላለች።
የ2024 ፕሬዝዳንታዊ ተወዳዳሪው ትራምፕም እሁድ እለት በፔንሲልቫኒያ የግድያ ሙከራ የቆሰለውን ጆሯቸውን እንደታሸጉ በቦታው መገኘታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
ዶናልድ ትራምፕ  በኮንቬንሽኑ ላይ ንግግር እንደሚያደርጉና የሪፐብሊካን ፕሬዝዳንታዊ ተወዳዳሪነታቸው በፓርቲያቸው እንደሚጸድቅላቸው ይጠበቃል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe