የገንዘብ ሚኒስቴር በወቅቱ ያልተሰበሰበ የማህበራዊ ልማት ቀረጥን በተመለከተ ውሳኔ አስተላልፏል

የገንዘብ ሚኒስቴር ለጉምሩክ ኮሚሽን በ 23/03/18 ዓም በጻፈው ደባዳቤ በወቅቱ ያልተሰበሰበ የማህበራዊ ልማት ቀረጥን በተመለከተ የታክስ ዕዳ ማቃለያ ውሳኔ  ሰጠ።

የማህበራዊ ልማት ቀረጥ ለትምህርት፣ ለስልጠና፣ እና ለጤና ተቋማት መልሶ ማቋቋሚያ እና ግንባታ እንዲሁም ለሌሎችም የማህበራዊ አገልግሎቶች ማስፋፊያ የሚውል የፋይናንስ ምንጭ እንዲያስገኝ በሚል ተግባራዊ የተደረገው ከሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ነው።

ነገር ግን ደንቡ ተግባራዊ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ መሰብሰብ የነበረበት የማህበራዊ ልማት ቀረጥ በወቅቱ ባለመሰብሰቡ ኮሚሽኑ(የጉምሩክ) ውዝፍ የታክስ ዕዳ እንዲከፈለው ዕቃዎችን ወደ አገር ያስገቡ አካላትን እየጠየቀ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ ተለዋጭ ውሳኔ እስኪሰጥ ዕዳውን የመሰብሰብ ሂደት ለጊዜው እንዲዘገይ በ17/4/2016 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ ማሳወቁን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውሷል።

ገንዘብ ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ ጉዳዩ ውሳኔ ሳያገኝ ተንጠልጥሎ መቆየቱ በኮሚሽኑ እና በግብር ከፋዮች መካከል የታክስ አስተዳደር ችግር እየሆነ መማጣቱን የጠቀሰ ሲሆን “ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ በማየት የታክስ ዕዳ ማቃለያ ውሳኔ መስጠቱ ተገቢ መሆኑ ታምኖበታል” ብሏል።

በውሳኔው መሰረት ፍሬ ግብሩ መከፈሉ እንደተጠበቀ ሆኖ:-

• በፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 648/2001 (እንደተሻሻለ) አንቀፅ 13(3) መሠረት በፍሬ ግብሩ ላይ የተጠየቀው ወለድ ቀሪ እንዲሆን፣

• መቀጫው እንዲነሳ፣

• እንዲሁም ፍሬ ግብሩን በአንድ ጊዜ መክፈል የማይችሉ ግብር ከፋዮች የክፍያ ስምምነት ውስጥ በመግባት በመመሪያው መሠረት የታክስ ዕዳቸውን በተራዘመ ጊዜ እንዲከፍሉ ተወስኗል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe