የጋዛን ተኩስ አቁም ተከትሎ የመጀመሪያዎቹ ታጋቾች እስረኞች ተለቀቁ

በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተደረሰው ተኩስ አቁም ዛሬ ሰኞም እንደጸና ነው። ሁለቱ ወገኖች ለስድስት ሳምንታት በሚዘልቀው ተኩስ አቁም የመጀመሪያ ምዕራፍ ላይ ሲኾኑ እ አ አ በ2023 ጥቅምት ወር ጀምሮ የቀጠለው ጦርነት ወደሚያከትምበት ጎዳና ሊያመራ እንደሚችል ተጠቁሟል።
በሐማስ ታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር ካሉት ታግቾች መካከል እስካሁን ሦስቱ የተለቀቁ ሲኾን ሌሎች ሠላሳ ታጋቾችን ደግሞ በዚሁ በመጀመሪያው የተኩስ አቁሙ ምዕራፍ ይለቀቃሉ።
እስራኤል በበኩሏ 90 ፍልስጥኤማዊያን እስረኞችን የለቀቀች ሲሆን ሁሉም ሴቶች እና ህጻናት መሆናቸውን ሃማስ አስታውቋል። እስራኤል በመቶዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ እስረኞች እንደምትልቅ ተመልክቷል።
ተኩስ አቁሙን ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም እጅግ አስፈላጊ የሆነውን የምግብ ርዳታ በብዛት ማስገባት ጀምሯል። በየቀኑ በጦርነቱ ምክንያት ኑሯቸው ለተመሳቀለባቸው ፍልስጥኤማዊያን ሲቪሎች የምግብ ርዳታ የጫኑ አንድ መቶ ሃምሳ መኪናዎችን እንደሚልክ አመልክቷል።
ትላንት የተኩስ አቁም ስምምነቱ ተግባራዊ መሆኑን ተከትሎ በሰዓታት ውስጥ ሃማስ የመጀመሪያዎቹን ሦስት ወጣት ሴቶች የለቀቀ ሲሆን ቀይ መስቀል ጋዛ በመግባት የተለቀቁትን ታጋቾች ተረክቧል። ሮሚ ጎኒን፥ ኤሚሊ ዳማሪ እና ዶራን ስታይንብሬከር የተባሉትን ታጋቾች እስራኤል አድርሷል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe