የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤትና በስሩ የሚገኙ 19 ተጠሪ ተቋማት የ2015 በጀት ዕቅዳቸውን አቀረቡ፡፡

ግንቦት 5 / 2014 ዓ.ም – የበጀት ዕቅዳቸውን ካቀረቡት ተቋማት መካከል የፌዴራል ስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ብቻ በተቀመጠለት የበጀት ጣሪያ መሰረት የ2015 በጀቱን አዘጋጅቶ ሲያቀርብ የተቀሩት ተቋማት በገንዘብ ሚኒስቴር ከተሰጣቸው ጣሪያ በላይ የበጀት ዕቅድ ይዘው ቀርበዋል፡፡
የበጀት ስሚ መርሀግብሩን የመሩት የገንዘብ ሚንሰትሩ ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ እንደገለጹት ከተሰጣቸው ጣሪያ በላይ የበጀት ጥያቄ ያቀረቡ ተቋማት ካለው የመንግስት ገቢ ውስንነትና ሌሎች ቅድሚያ ከሚያስፈልጋቸው ስራዎች አኳያ ከጣሪያ በላይ የበጀት ጥያቄ ያቀረቡ ተቋማት የበጀት እቅዳቸውን በጥቂት ቀናት ውስጥ አስተካክለው እንዲያቀርቡ አመራር ሰጥተዋል፡፡
በአቅም ውስንነት ምክንያት በ2015 በጀት አመት አዳዲስ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ እንደማይደረጉ ጠቁመው ይልቁንም ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እንዲቻል ተቋማት ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ በሚያስችል መልኩ የበጀት ጥያቄያቸውን ማቅረብ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
የገንዘብ ሚንስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ በበኩላቸው ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የሆነው የአደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ከስራው ባህሪ አንፃር ያለበትን የኦዲት ችግር ለመፍታት የተለየ ውይይት እንደሚመቻች አመልክተው ተቋሙ እራሱን በመገምገም ችግሮቹን ለመፍታት ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe