የጤፍ የባለቤትነት ጥያቄ ክስ በገንዘብ እጥረት ሳቢያ መመስረት አልተቻለም ተባለ

‘ኔዘርላንድስ እና ጀርመንን ጨምሮ 3 ሀገራት የባለቤትንት መብቱ የኛ ነው በሚል መከራከሪያ አንስተዋል።’

ከጤፍ የባለቤትነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ የኔዘርላንድስ ድርጅትን ለመክሰስ ዝግጅት እየተደረገ ቢሆንም በገንዘብ እጥረት መክንያት ክሱ አለመመስረቱን የኢትዮጵያ ብዝኃ ህይወት ኢንስቲትዩት ገለፀ።
ለምርምር ተግባር በሚል ከኔዘርላንድስ ኩባንያ ጋር በተገባ ስምምነት ወደ ኔዘርላንድስ የተወሰደው የኢትዮጵያ ጤፍ የባለቤትነት ጥያቄን ማስነሳቱ ይታወሳል።

Read also:የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአስሩ የአፍሪካ ምርጥ ብራንድ ድርጅቶች ብቸኛው አፍሪካዊ…

ይህንን ተከትሎ ኔዘርላንድስ እና ጀርመንን ጨምሮ 3 ሀገራት የባለቤትንት መብቱ የኛ ነው በሚል መከራከሪያ አንስተዋል። የአውሮፓ አዕምሮአዊ ጽህፈት ቤት ለኔዘርላንድስ የባለቤትን ማረጋገጫ መስጠቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ የኔ ነው የሚል ክርክር አንስታለች።
ይሁን እንጂ በድርድር መስማማት ባለመቻሉ ጉዳዩ በፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ተይዞ ወደ ክስ ሂደት ሊያመራ መሆኑን የኢትዮጵያ ብዝኃ ህይወት ኢንስትትዩት ለአሐዱ ቴሌቭዥን አብራርቷል። ሆኖም ጉዳዩ ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቅ በመሆኑ መንጓተቱን ኢንስቲትዩቱ ይገልፃል።

Read also:በኢትዮጵያ በአራት አመት ውስጥ 20 ቢሊዮን ችግኝ የመትከል ዕቅድ መኖሩን ጠቅላይ…

ከጤፍ የተወሰኑ ምርቶችን ማምረት ከተሳካለት የኔዘርላንድስ ኩባንያ ጋር የጥቅም መጋራት ውል ተፈጽሞ ወደ ስራ መግባቱን የሚያስታውሰው ኢንስቱትዩቱ፤ ኢትዮጵያም ምንም ጥቅም ማግኘት አለመቻሏን ያብራራል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe