የፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎት የውርስ ማስረጃ መያዝ ብቻውን የውርስ ተካፋይ አያደርግም የሚል ውሳኔ ማሳለፉ ታውቋል፡፡
ከወራሽነት ማስረጃ ጋር በተገናኘ የፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎት አዲስ የህግ ትርጉም መስጠቱ ተነግሯል፡፡ ይሔው አዲስ የህግ ትርጉምም የወራሽነት ማስረጃ መያዝ ብቻውን የውርስ ተካፋይ እንደማያደርግ ገልጻል፡፡
የውርስ ማስረጃ የያዘ ሰው እስከ ሦስት ዓመት ጊዜ ብቻ ነው የውርስ ሃብት መብቱን መጠየቅ የሚችለው ተብሏል፡፡ በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ የውርስ ክፍፍል ጥያቄውን ማቅረብ ካልቻለ ጥያቄው በይርጋ ውድቅ ይሆናል፤የውርስ ሃብት መካፈልን መብትንም ያጣል የሚል የህግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡
የወራሽነት ማስረጃ የያዘ አካል በሦስት ዓመት ውስጥ የመብት ጥያቄ ካላቀረበ የውርስ ሃብት መካፈልን መብትንም ያጣል የሚል ትርጉም ሰጥቷል፡፡
የወራሽነት ማስረጃ ወረቀት ብቻ መያዝ በማንኛውም ጊዜ የውርስ ድርሻ ለመጠየቅ እንደማያስችል ተመላክቷል፡፡

