የገቢዎች ሚኒስቴር ያለ ሐኪም ትዕዛዝ ከሚሸጡ መድኃኒቶች ተጨማሪ ቫትን ሰብስበው ገቢ የማያደርጉ ፋርማሲዎችና አቅራቢዎች ተጣርተው ዕርምጃ እንዲወሰድባቸው ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ መሠረት ወደ አገር ውስጥ ከሚገቡ መድኃኒቶች መካከል ያለ ሐኪም ትዕዛዝ የሚሸጡ የመድሃኒት አይነቶች ታክስ እንዲጣልባቸው ተደንግጓል፡፡
አዲሱ አዋጅ ሲዘጋጅ በቀድሞው አዋጅ ከቫት ነጻ ተደርገው የነበሩ መድኃኒቶች ውስጥ ያለ ሐኪም ትዕዛዝ የሚሸጡ መድሃኒቶች ይገኙበታል፡፡
ሚኒስቴሩ ቫት እንዲጣልባቸው ያለ ሐኪም ትዕዛዝ የሚሸጡ የመድኃኒት ዓይነቶችን ዝረዝር ለይቶ እንዲያቀርብ፤የኢትዮጽያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣንን በጠየቀው መሠረት ዝርዝራቸው ተለይቷል፡፡
በህብረተሰቡ ዘንድ በብዛት ጥቅም ላይ የሚው እንደ ህመም ማስታገሻ ያሉት መድኃኒቶች በዝርዝሩ ውስጥ ተካተዋል መባሉን የሪፖርተር ዘገባ ያመላክታል፡፡//

