የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ጨምሮ ከፍተኛ ባለሀብቶችን ይዞ ለመመስረት የአክሲዮን ሽያጭ እያደረገ የነበረው ዳሎል ባንክ ለምስረታ የሚያስፈልገውን ካፒታል አሟልቶ ቢቀርብም ላለፉት 18 ወራት ብሔራዊ ባንክ ምላሽ ሳይሰጥ ቆይቶ በስተመጨረሻ አልመዘግብም ማለቱ ተሰምቷል፡፡ የዳሎል ባንክ ምስረታ አመቻች ኮሚቴ የአንድ አክሲዮን ዋጋን ብር አንድ ሺ አድርጎ አነስተኛ የአክሲዮን ግዢን 25 ሺ ብር ከአምስት ከመቶ የአገልግሎት ክፍያ ጋር በመጠየቅ ማስታወቂያ ቢያወጣም በአጭር ጊዜ የሚፈለገው ብር ተሟልቷል፡፡ነገር ግን ብሔራዊ ባንክ የዳሎል ባንክ ከፍተኛ ባለአክሲዮን የሆነችው ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በንግድ ስራ ውስጥ የመግባቷ ተገቢነት ላይ ጥያቄ እንዳለው ታውቋል፡፡ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው አዲስ መመሪያ መሠረት አዲስ ባንክ ለመመስረት የሚያስፈልገው የተከፈለ ካፒታል ቢያንስ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲሆን የወሰነ ሲሆን ዳሎል ባንክ በዚህ ረገድ በአጭር ጊዜ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ማሰባሰብ መቻሉን ምንጮች ተናግረዋል፤ በባንኩ የመመስረቻ ፅሑፍ ላይ እንደተመለከተው ከሆነ ባንኩን ለመመስረት ብሔራዊ ባንክ ካስቀመጠው ጣራ በላይ በማለፍ 2 ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር ለማሰባሰብ እቅድ ይዞ የነበረ የተነሳው ዳሎል ባንክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስተያንን ጨምሮ መስራቾቹ እያንዳንዳቸው ቢያንስ የ100 ሚሊዮን ብር አክሲዮን ለመክፈል ከስምምነት ላይ ደርሰዋል ተብሎ ነበር፤ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በአራት የልማት ድርጅቶቿ የብር 400 ሚሊዮን ብር አክሲዮን ገዝታ የገባች ሲሆን ቀሪው የዳሎል ባንክ የአክሲዮን አባላት በሀገሪቱ አሉ የተባሉ 18 ባለሀብቶችን የአንድ ቢሊዮን 800 ሚሊዮን ባለድርሻዎች ነበሩ፡፡ይህ የአክሲዮን ሽያጭ በአጭር ቀናት ተካሂዶ መስከረም 30 ቀን 2010 ዓ.ም መዘጋቱ ታውቋል፡፡ ብሔራዊ ባንክ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የባንኩ አደራጅ ኮሚቴዎች ገንዘቡን በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ለባለአክሲዮኖች ተመላሽ ማድረግ መጀመራቸው ታውቋል፡፡
ይልቅ ወሬ ልንገርህ:- በምስረታ ላይ የነበረውን ዳሎል ባንክ ብሔራዊ ባንክ አልመዘግብም አለው
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

