ዳሸን ባንክና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ዘላቂ የአረንጓዴ ልማት ፋይናንስ አገልግሎት ፕሮጀክት ማስጀመሪያ ጉባኤ አካሄዱ

ዳሸን ባንክ ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ጋር በመተባበር ለዘላቂ የአረንጓዴ ልማት የሚቀርብአገልግሎት ፕሮጀክት ማስጀመሪያ ጉባኤ አካሂዷል፡፡
የሁለቱ ባንኮች ተወካዮች ዛሬ በዳሸን ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ባካሄዱት ጉባኤ የአየር ንብረት ለውጥ በፋይናንስ ኢንዱስትሪው አጠቃላይ አገልግሎት ላይ ስለሚያስከትላቸው ተፅዕኖዎችና አደጋዎች ይህን ከግምት ውስጥ ያስገባ አሰራርና አገልግሎት መፍጠር ላይ ያተኮረ እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ በአሁኑ ወቅት የባንኮች ሚና ብድር ማቅረብና ተቀማጭ መሰብሰብ ብቻ ሳይሆን የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከልና ተግዳሮቶችን ለመቋቋም ለሚያስችሉ ስራዎች የፋይናንስ አገልግሎት መስጠትን እንደሚጨምር አስገንዝበዋል፡፡ ባንኮች ለአረንጓዴ ልማትና ዘላቂ ከባቢያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ኢንቨስትምነቶችን ማበረታታት እንደሚገባቸውም አመልክተዋል፡፡
አቶ አስፋው ዳሸን ባንክ ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ጋር በመተባባር አረንጓዴ፣ አካታችና የአየር ንብረት ለውጥ ተፅኖዎችን መቋቋም ለሚያስችሉ ፕሮጀክቶች
የፋይናንስ አገልግሎት የማቅረብ አቅሙን ይበልጥ እንደሚያጎለብት ተናግረዋል፡፡
የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ዓለም አቀፍ ዳይሬክቶሬት የኢንቨስትመንት ኦፊሰር ቶማስ ሉጌዝ በበኩላቸው ዳሸን ባንክ የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ከኢትዮጵያከመረጣቸው አጋሮች አንዱና ተገቢው አጋር መሆኑን ጠቁመው የሚሰጠው የቴክኒክ ድጋፍም በኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት ፋይናንስ አገልግሎቶችን ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚያግዝ አመልክተዋል፡፡ ይህ የቴክኒክ ድጋፍ መስጠት ፕሮጀክት ሁለቱ ባንኮች ለወደፊት በመካከላቸው ያለውን ግንኙነትና ትብብር ለማጠናከርና በጋራ ለመስራትዕድል የሚፈጥር መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
በውይይቱ ላይ በአውሮፓእንቨስትመንት የቴክኒክ ድጋፍ እንዲሰጥየተመረጠው አማካሪ ድርጅት በኩል ለዳሸን ባንክ በሚሰጠው የቴክኒክ ድጋፍ ዙሪያ የተለያዩ ጉዳዮች ተነስተውውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
ሁለቱ ባንኮች የሚተገብሩት ፕሮጀክት ዳሸን ባንክ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘሊከሰቱ የሚችሉ ተግዳሮቶችን ይበልጥ መቋቋም እንዲችልና የሚሰጣቸው የፋይናንስ አገልግሎቶችም ከዚህ አንፃር የተቃኙ እንዲሆኑየሚያስችል መሆኑ ተመልክቷል፡፡
ፕሮጀክቱ ዳሸን ባንክ ለአረንጓዴ ልማት የሚሰጠውን የፋይናንስ አገልግሎትና የብድር አቅርቦት ይበልጥ የሚያጎለብት እንደሚሆንም በውይይቱ ተነስቷል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe