ድምጻዊ ጎሳዬ ተስፋዬ  ከህመሙ አገግሞ ከአንድ ወር በኋላ ወደ ስራ እንደሚመለስ ተገለፀ

ድምጻዊ ጎሳዬ ተስፋዬ ለንደን ሄትሮ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ አዳልጦት በመውደቁ ወለም እንዳለው ታወቀ፡፡

​ተወዳጁ ድምጻዊ ጎሳዬ ተስፋዬ በሀገረ እንግሊዝ የነበረውን የሙዚቃ ኮንሰርት አጠናቆ ተላንት ጠዋት ወደ ሀገሩ ሲመለስ ሄትሮ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ አዳልጦት በመውደቁ ወለም ብሎታል፡፡

አርቲስት ጎሳዬ ወደ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ወለምታው አላራምድ ስላላው በዊልቼር ላይ ተቀምጦ ወደ ቤቱ ለመሄድ መገደዱን ታዲያስ አዲስ ዘግቧል።

በአሁኑ ሰዓት ጎሳዬ ህክምናውን በቤተሳይዳ ሜዲካል ሴንተር እየተከታተለ ሲሆን ከአንድ ወር በኋላ ወደ ስራው ሙሉ ለሙሉ እንደሚመለስ ታውቋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe