ግብጽ በሱዳን ድንበር አቅራቢያ በድሮን የታገዘ ጥቀት አደረሰች፡፡ በዚህ የድሮን ጥቃትም በርካቶች መገደላቸው ተነግሯል፡፡
በሱዳን ናይል ግዛት ከግብጽ ድንበር አቅራቢያ በሚገኙ የባህላሊ ወርቅ ማውጫ ስፍራዎች ላይ ማክሰኞ ዕለት በተፈጸመ የድሮን እና ከባድ መሳሪያ ድብደባ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል፡፡ ሌሎች ደግሞ መቁሰላቸው ታውቋል፡፡
ማዕድን አውጪዎቹ ጥቃቱን የሰነዘረው የግብጽ ጦር መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዚሁ በማዕድን ማውጫ ስፍራ አቅራቢያ የግብጽ ወታደራዊ የጦር ሰፈር ይገኛል፡፡
ይህ ቀጠና ባለፉት ወራት ውስጥ ተደጋጋሚ ፍጥጫዎች ሲስተናገዱበት የቆየ ስፍራ መሆኑን ዘገባው አትቷል፡፡ ከዚህ ቀደም የግብጽ ድንበር ጠባቂዎች የማዕድን ማውጫ መሳሪያዎችን እና በስፍራው የሚገኙ መጠለያዎችን አውድመዋል፡፡
የግብጽ ባለስልጣናት ለተነሳቸው ክስ የሱዳን ማዕድን አውጪዎች ድንበር ጥሰው በመግባት ቆፋሮ አድርገዋል ብለዋል፡፡ የሱዳን ትሪቡን ዘገባ በግብጽ ጥቃት የተገደሉት በርካታ ናቸው ከማለት ባለፈ ስለ ቁጥሩ የጻፈው ነገር የለም፡፡//

