ግብፅ ጅቡቲን ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ጥገኝነት ያላቅቃል ያለችውን የጸሐይ ሐይል ፕሮጀክት ልትገነባ ነው።

ግብፅ ጅቡቲን ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ጥገኝነት ያላቅቃል ያለችውን የጸሐይ ሐይል ፕሮጀክት ልትገነባ ነው።
ጅቡቲ እና ግብፅ በጅቡቲ 276.5 ኪሎ ዋት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ለመገንባት የሚያስችል ታሪካዊ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት እያጠናከረ የጅቡቲን የኢነርጂ ነፃነት እንደሚያሳድግ ይጠበቃል ተብሏል።
የግብፅ ኤሌክትሪክ እና ታዳሽ ኢነርጂ ሚኒስትር ማህሙድ እስማት እና የጅቡቲ የኢነርጂ እና የተፈጥሮ ሃብት ሚኒስትር ዮኒስ አሊ ጉሌድ ስምምነቱን የተፈራረሙት በግብፅ በተዘጋጀ መደበኛ ስነ-ስርዓት ላይ ነው።
ፕሮጀክቱ ሙሉ ለሙሉ በግብፅ የገንዘብ ድጋፍ ይገነባል የተባለ ሲሆን፤ጅቡቲ የኃይል ምንጭ አማራጮቿን በማብዛት ከኢትዮጵያ በምታስገባው የኤሌክትሪክ ኃይል ላይ ያላትን ጥገኝነት በመቀነስ አገሪቱን በኢነርጂ ራሷን እንድትችል ያደርጋታል ተብሏል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe