የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ስታርመር በትራምፕ ዛቻ እንደማይንበረከኩ ገለጹ፡፡
የዩኬው ጠቅላይ ሚኒስትር በኢራን የሚካሄደውን ጦርነት እንዲቀላቀሉ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለሚደርስባቸው ጫና እንደማይንበረከኩ ነው ያስታወቁት፡፡
ስታርመር ይህንን ያሉት ትራምፕ ለስካይ ኒውስ በሰጡት ቃል መጠይቅ አሜሪካ የዩናይትድ ኪንግደምን እርዳታ በጠየቀችበት ወቅት አልተገኘችም ካሉ በኋላ ነው፡፡
ትራምፕ አክለውም ከዩኬ ጋር የተደረሰው የታሪፍ ስምምነት መቼም ቢሆን ሊቀየር ይችላል ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፓርላማው ባደረጉት ንግግር ሃሳቤን አልቀይርም፡እጅ አልሰጥም፡ጦርነቱን መቀላቀል ብሔራዊ ጥቅም አይደለም ስለዚህም አናደርገውም ሲሉ አቋማቸውን ግልጽ አድርገዋል፡፡
በኢራን ላይ ያለኝ አቋም ግልጽ ነው እዚህ ጦርነት ውስጥ ተገደን አንገባም በማለት ተናግረዋል፡፡ የእኛ ጦርነት አይደለም፡የተለየ አቅጣጫ እንዲይዝ ብዙ ጫና ተደርጎብኛል ብለዋል፡፡
ትራምፕ በሰጡት ኢንተርቪው እገዛ ስንጠይቃቸው አልተገኙም፡እንዲህ አይነት ግንኙነት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚስትር ስታርመር በጦርነቱ ውስጥ ቀጥታ እንዲሳተፉ የቀረበላቸውን ጥሪ ውድቅ ማድረጋቸውን ተከትሎ ከትራምፕ ተደጋጋሚ ትችት ደርሶባቸዋል፡፡//

