ፀሐይ ባንክ አ.ማ ጠቅላላ ሀብቱ 3.5 ቢሊዮን መድረሱን አስታወቀ

የፀሐይ ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ተካሔደ
በዛሬው እለት ታህሳስ 18 ቀን 2016 በሸራተን ሆቴል ጉባዔውን በንግግር የከፈቱት የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ታዬ ዲበኩሉ የባንኩን የ2022/23 ዓመታዊ ሪፖርት ለባለአክሲዮኖች አቅርበዋል።
ባንኩ ዘመናዊ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉትን በርካታ ቅርንጫፎች መክፈት፣ የቴክኖሎጂዎች ግዢ መፈፀም እና የሠራተኞች ቅጥር ማናከናወን ሥራዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ በመስራት ውጤታማ መሆን እንደቻለ በመድረኩ ተነስቷል፡፡
በዚህም የባንኩ ጠቅላላ ሀብት ሰኔ 30/2023 ላይ ብር 3.5 ቢሊዮን መድረሱን የገለጹት የቦርድ ሊቀመንበሩ፤ የደንበኞች ቁጥር ጥሩ እድገት በማሳየት 229 ሺህ ማለፉን ጠቁመዋል፡፡
ባንኩ በተቋቋመ አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በተለይ የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት እና ዘመኑን የዋጁ የባንክ ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ ስኬታማ እንደነበር አቶ ታዬ ዲበኩሉ አስረድተዋል፡፡
ባንኩ የማኅበራዊ ትስስር መረብ የባንክ አገልግሎት (Social Media Banking) ጨምሮ የተለያዩ የዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች ለተጠቃሚዎች እየሰጠ እንደሚገኝ የጠቆሙት ሊቀመንበሩ፤ የክሬዲት ካርድ አገልግሎት መጀመሩንም ተናግረዋል፡፡
በ2022/23 የውጭ ኦዲተሮች ሪፖርት ላይ ውይይት ተደርጎ ሰነዱ የፀደቀ ሲሆን፤ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫም ተከናውኗል፡፡
ገበያ ማስፋፋት፣ ከዓለም አቀፍ ባንኮች እና ከአጋር አካላት ጋር ያለን ግንኙነት ማጠናከር፣ አነስተኛ ብድር አቅርቦትን ማጎልበት፣ አዳዲስ አገልግሎቶች ማስተዋወቅ እንዲሁም የካፒታል አቅምን በማሳደግ በቅርቡ ክፍት ለሚሆነው የካፒታል ገበያ መዘጋጀት የባንኩ የትኩረት አቅጣጫዎች እንደሚሆኑ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ያሬድ መስፍን ገልፀዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe