ፌስቡክ ኩባንያ ከኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ጋር በተያያዘ ሐሰተኛ ገጾች እና አካውንቶች ዘጋ

ፌስቡክ ኩባንያ በመጭው ሰኞ ከሚደረገው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ጋር በተያያዘ በተቀናጀ መንገድ የሚሰሩ ያላቸው ሐሰተኛ ገጾች እና አካውንቶች መዝጋቱን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

የተዘጉት አሳሳችና ሐሰተኛ መረጃ ያሰራጩ 64 የፌስቡክ አካውንቶች፣ 52 የፌስቡክ ገጾች፣ 27 የቡድን ስብስቦች እና 32 የኢንስታግራም አካውንቶች ናቸው። አካውንቶቹ ከብልጽግና ፓርቲ እና ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ጋር የተያያዙ ጽሁፎችን ያወጡ እና ኦነግን እና ሕወሃትን ጨምሮ የተለያዩ ፖለቲካ ድርጅቶችን እና አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ የሚተቹ ጽሁፎችን ያሰራጩ እንደነበር መግለጫው ጠቅሷል። አካውንቶቹ በኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ውስጥ ካሉ አንዳንድ ግለሰቦች ጋር የተያያዙ እንደሆኑ ኩባንያው አክሎ አመልክቷል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe