ፍላይዱባይ በአቪዬሽን ፈጠራ ዘርፍ  የ2024 ሁለት ሽልማቶች  አሸናፊ ሆነ

መቀመጫውን በዱባይ ካደረገው አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት በ9ኛው  በአቪዬሽን ፈጠራ ሽልማቶች ውድድር በአየር መንገድ ኢንዱስትሪ ዘርፍ በ “ልዩ ምርቶች እና አገልግሎቶች ፈጠራ” እና በአየር ጭነት እና ሎጅስቲክስ ምድብ “ፈጠራ ትብብር እና አጋርነት” ፍላይዱባይ አየር መንገድ ሁለት እውቅና ማግኘቱ ታወቀ።

የአቪዬሽን ፈጠራ ሽልማቱ የአቪዬሽን ዓመታዊ የውድድር ሽልማት አካል ሲሆን የ 2024 ፕሮግራም በቴክኖሎጂ፣ በዘላቂነት፣ በአሰራር፣ በምርት ልማት፣ በአገልግሎቶች፣ በምህንድስና እና በአመራር ላይ ልዩ የአቪዬሽን ፈጠራዎችን ያበረታታል።

የፍሊዱባይ ዋና የፋይናንስ ኦፊሰር ሚስተር ፍራንኮይስ ኦበርሆልዘር በሽልማቱ ላይ እንደገለጹት፡– “ፍላይዱባይ  ለፈጠራ እና ለኢንቨስትመንት ምርት ልማት ባለው ቁርጠኝነት ባለፉት ዓመታት ከፍተኛ እድገት አሳይቷል።  ሁልጊዜም ለደንበኞቻችን የምናቀርበው አገልግሎት  በመሬት ላይም ሆነ በአየር ላይ ምቶትን ያስቀድማል፤› ብለዋል፡፡

ፍላይዱባይ በጥቅምት 2024  አዲሱን የመንገደኞች  የቢዝነስ ክፍል ማስተናገጃ  ተርሚናል 2 በዱባይ ኢንተርናሽናል አየር መንገድ (DXB) ላይ በይፋ አስጀምሯል፣ በዚህ የተነሳ በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ ፍላይዱባይ በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ በAPEX የባለ አራት ኮከብ ሜጀር አየር መንገድ ደረጃን አግኝቷል።

በፍላይዱባይ የኤርፖርት ሰርቪስ እና ጭነት ከፍተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት መሀመድ ሀሰን “የፈጠራ ትብብር እና አጋርነት” ሽልማት በማግኘታችን ደስ ብሎናል። ከ 2012 ጀምሮ ደንበኞቻችንን በተሻለ ሁኔታ ለማገልገል እና ነፃ የንግድ ፍሰት ለመፍጠር የእኛን የአሠራር ችሎታዎች ለማዳበር ቆርጠን እየሰራን ነው። አጋርነታችንን በማጠናከር እና በመጨረሻዎቹ ቴክኖሎጂዎች ላይ ኢንቨስት በማድረግ የካርጎ ኦፕሬሽን ተደራሽነት ማዳበርን እንቀጥላለን፤ የዱባይን እንደ መሪ አለምአቀፍ የአቪዬሽን ማዕከል እናረጋግጣለ ብለዋል፡፡

ስለ ፍላይዱባይ

እ.ኤ.አ. በ 2012 አገልግሎት መስጠት የጀመረው ፍላይዱባይ ካርጎ በ 53 አገሮች ውስጥ ከ 150 በላይ መዳረሻዎችን ያሉት  ዓለም አቀፍ ኦፕሬሽን አለው ፣ ይህም ከዱባይ በርካታ የበረራ አገልግሎቶችን አስተማማኝ በማድረግ  ምቾት ይሰጣል ። ዱባይ ከደረሰ በኋላ በአንድ ሰአት ውስጥ ከአንድ የፍላይዱባይ የጭነት  በረራ ወደ ሌላ ማጓጓዝ ይችላል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe