ፎረፎርን በዘላቂነት ለማጥፋት የሚረዱ 10 ዘዴዎች

ፎረፎርን በተፈጥሯዊ እና በቀላል የቤት ውስጥ መላዎች ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ማስወገድ ይቻላል። የፎረፎር ዋነኛ ምልክቶች በፀጉር ሥር የሚታዩ ነጫጭ ቅርፊቶች እና ከፍተኛ የማሳከክ ስሜት ናቸው። ፎረፎር በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል።

  • ውጥረት (Stress)
  • የተመጣጠነ ምግብ እጥረት
  • የፈንገስ ኢንፌክሽን
  • ፀጉርን አዘውትሮ አለመታጠብ
  • የተወሰኑ መድኃኒቶች ጭምር ፎረፎርን ሊያስከትሉ ይችላሉ። ፎረፎርን በዘላቂነት የሚያጠፉ 10 ምርጥ ዘዴዎች
  1. ሬት ለፎረፎር (Aloe Vera) አንድ የሾርባ ማንኪያ ንጹሕ የሬት ጄል ላይ የግማሽ ሎሚ ጭማቂ ጨምረው እንደ ፀጉር ማስክ ይቀቡት። ሬትም ሆነ ሎሚ ፎረፎርን የሚያስከትሉ ባክቴሪያዎችን እና ፈንገሶችን በፍጥነት በመዋጋት ፎረፎርን ለማከም ይረዳሉ።
  2. አብሽ (Fenugreek) አንድ የሾርባ ማንኪያ የአብሽ ዱቄት ላይ በቂ እርጎ በመጨመር ለ30 ደቂቃ ያህል ያስቀምጡት። ይህም አብሹ እንዲወፍር ይረዳዋል። በደንብ ከመቱት በኋላ እንደ ፀጉር ማስክ ይጠቀሙ። (ይህ ውህድ የሳይነስ ችግር ላለባቸው ሰዎች አይመከርም)።
  3. የኒም ቅጠል ውህድ (Neem Rinse) አንድ ጥቅል የኒም ቅጠልን ከውኃ ጋር አፍልተው የውኃው ቀለም ሲቀየር ያውጡት። ከቀዘቀዘ በኋላ አጥልለው የግማሽ ሎሚ ጭማቂ ጨምረውበት ፀጉርዎን ለመጨረሻ ጊዜ ይለቃለቁበት። ይህ ውህድ ፎረፎርን ለማጥፋት በጣም ውጤታማ ነው።
  4. አምላ ለፎረፎር (Amla) አንድ የሾርባ ማንኪያ የአምላ ዱቄት ላይ ንጹሕ የሬት ጄል ቀላቅለው እንደ ማስክ ይቀቡት። ለ20 ደቂቃ አቆይተው በሻምፖ ይታጠቡ። ይህ ማስክ ፎረፎርን ከማጥፋቱም በላይ የፀጉር እድገትን ያበረታታል። 5.የአፕል ሳይደር ኮምጣጤ እና ሎሚ (Apple Cider Vinegar & Lemon) እኩል መጠን ያለው የሎሚ ጭማቂ እና የአፕል ሳይደር ኮምጣጤ ይቀላቅሉ። ከዚያ አንድ የሾርባ ማንኪያ ከዚህ ውህድ ወስደው ከአንድ ኩባያ ውኃ ጋር በመበጥበጥ ፀጉርዎን ይለቃለቁበት። ይህ ፎረፎርን ለማከም አስደናቂ መላ ነው። 6.የሎሚ እና የኮኮናት ዘይት (Lemon & Coconut Oil) አንድ የሾርባ ማንኪያ የኮኮናት ዘይት ላይ እኩል መጠን ያለው የሎሚ ጭማቂ ጨምረው ያዋህዱ። በጥጥ እየነከሩ የራስ ቅልዎን በደንብ ይቀቡት። ለ15 ደቂቃ አቆይተው ይታጠቡ። ማሳከክን በመጀመሪያ ዙር ሲጠቀሙት ያስቆማል፤ ደጋግመው ሲጠቀሙት ደግሞ ፎረፎሩ ሙሉ በሙሉ ያጠፋል። 7.የጥብስ ቅጠል ውህድ (Rosemary Rinse) የጥብስ ቅጠል (Rosemary) ለፀጉር ጤንነት በሀገራችን በስፋት ከሚታወቁ መላዎች አንዱ ነው። ጥቂት የጥብስ ቅጠሎችን በውኃ ውስጥ ለጥቂት ደቂቃዎች ያፍሉት። ውኃው ከቀዘቀዘ በኋላ አጥልለው ፀጉርዎን ከታጠቡ በኋላ በመጨረሻ ይለቃለቁበት። ፎረፎርን ከመከላከልም ባሻገር ለፀጉርዎ ጥሩ ልስላሴ ይሰጣል። 8.እንቁላል እና የኮኮናት ዘይት (Egg & Coconut Oil) የእንቁላል ማስክ ፎረፎርን ለማከም በጣም ጥሩ ነው። አንድ እንቁላል ሠብረው ከአንድ የሻይ ማንኪያ ንጹሕ የኮኮናት ዘይት ጋር በደንብ ይምቱት። ይህንን ውህድ በብሩሽ ፀጉርዎን ተቀብተው ለ15 ደቂቃ ያህል ካቆዩ በኋላ ይታጠቡት።
  5. የሻይ ዛፍ ዘይት (Tea Tree Oil) ይህ ዘይት ፎረፎርን የሚያስከትሉ ፈንገሶችን እና ባክቴሪያዎችን በመዋጋት ይታወቃል። 3 ጠብታ የሻይ ዛፍ ዘይትን ከአንድ የሾርባ ማንኪያ የኮኮናት ዘይት ጋር ቀላቅለው የራስ ቅልዎን ይቀቡ። ለተሻለ ውጤት በሳምንት ሁለት ጊዜ ይጠቀሙ። 10.የከሪ ቅጠል (Curry Leaf) (ማሳሰቢያ:- ይህ ቅጠል በሀገራችን የተለመደ አይደለም፤ ነገር ግን በውጭ ሀገራት ለሚኖሩ ወይም በልዩ መደብሮች ለሚያገኙት ይጠቅማል)። አንድ እፍኝ የከሪ ቅጠልን ከእርጎ እና ከጥቂት የሎሚ ጭማቂ ጋር በመፍጨት እንደ ማስክ ይጠቀሙ። በሳምንት ሦስት ጊዜ በመጠቀም አስደናቂ ለውጥ ያያሉ። (Ethio Tena)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe