ፑቲን ለ5ኛ የስልጣን ዘመን አሸነፉ

ቭላድሚር ፑቲን ለቀጣይ 6 ዓመታት ሩስያን መምራት የሚያስችላቸውን የምርጫ ውጤት ማስመዝገባቸው ተነገረ።
ሩስያን በፕሬዜዳንትነት እየመሩ የሚገኙት የቀድሞው የKGB ሰላይ ቭላድሚር ፑቲን በሀገራቸው የተካሄደውን የፕሬዜዳንታዊ ምርጫ በከፍተኛ ብልጫ ማሸነፋቸውን ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ባለፉት 3 ቀናት በመላ ሩስያ ህዝቡ ድምፅ ሲሰጥ ቆይቷል።
የ71 ዓመቱ ፑቲን ” ጠንካራ ተቀናቃኝ አልገጠማቸውም ” በተባለው በዚህ ምርጫ ከ87% በላይ ድምፅ በማግኘት ሀገሪቱን በፕሬዜዳንትነት መምራት እንዲቀጥሉ የሚያስችላቸውን ውጤት እንዳገኙ ተገልጿል።
ፑቲን የ2024ቱ ምርጫ ለ5ኛ የስልጣን ዘመን ያሸነፉት ምርጫ ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe