ፕሬዝዳንት ትራምፕ በግሪንላንድ የአሜሪካን ሰንደቅዓላማ ሲሰቅሉ የሚያሳይ የኤአይ ምስል በማህበራዊ ገጻቸው ላይ ለጠፉ

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ግሪንላንድን ወደ አሜሪካ ለመጠቅለል ሊወስድት የሚችሉት እርምጃ ምን ሊሆን እንደሚችል እየተጠበቀ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ግሪላንድን ለመቆጣጠር የሚደረገው ጉዞ በምንም ሁኔታ ወደ ኋላ የለም ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ግሪንላንድን ወደ አሜሪካ ለመጠቅለል ሊወስድት የሚችሉት እርምጃ ምን ሊሆን እንደሚችል እየተጠበቀ ነው፡፡ ሁሉም ዲፕሎማሲያዊ መንገዶች ከጠረጼዛው ላይ ተነስተዋል የተባለ ሲሆን ቀጣዩ እርምጃ ወታደራዊ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዳግመኛ ወደ ዋይት ሐውስ መንበራቸው ከተመለሱ አንድ ዓመታቸውን ደፍነዋል፡፡ በዚህ አንድ ዓመት የስልጣን ቆይታቸውም በርካታ ያልተጠበቁ ውሳኔዎችን ወስነዋል፡፡ ከሁሉም ግን ሰሞንኛ መነጋገሪያ የሆነውና ሦስቱን ሃያላን ሀገራት እንዲሁም መላው አውሮፓን እያነጋገረ ያለው ግሪንላንድን ወደ አሜሪካ የመጠቅለሉ ጉዳይ ነው፡፡

ትላንትናም ፕሬዝዳንት ትራምፕ አንድ ብዙዎችን ያነጋገረ የኤአይ ምስል በማህበራዊ ገጻቸው ላይ ለጥፈዋል፡፡ ይህ ምስል እሳቸው በግሪንላንድ የአሜሪካን ሰንደቅዓላማ ሲሰቅሉ የሚያሳይ ነው፡፡

ትራምፕ እንዲህ አይነቱን ተግባር ሲፈጽሙ የአሁኑ የመጀመሪያቸው አይደለም፡፡ ከወራቶች በፊት እንዲሁ ካናዳ የአሜሪካ እንዷ ግዛት መሆኗን የሚያመላክት ምስል ማጋራቸው አይዘነጋም፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ አሜሪካ ግሪንላንድን የግድ መጠቅለል እንዳለባት ያምናሉ፡፡ ትራምፕ ከዚህ ቀደም ዴንማርክ ግሪንላንድን ለአሜሪካ እንድትሰጣት ነበር የጠየቁት አሁን ግን ዴንማርክም ግሪንላንድን የመቆጣጠር ህጋዊ መብቱ የላትም ወደማለት መጥተዋል፡፡

ትራምፕ ግሪንላንድን በአሜሪካ ቁጥጥር ስር ማስገባት እጅግ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ደግመው ተናግረዋል፡፡

የግሪንላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር፡የዴንማርክ መንግስት፡አውሮፓ እና ግሪንላንዳዊያን የፕሬዝዳንት ትራምፕን እንቅስቃሴ በማውገዝ ላይ ናቸው፡፡ እናም ሁሉም ዲፕሎማሲያዊ መንገዶች ከምርጫ ውጪ መሆናቸውን የሚያመላክቱ ሁኔታዎች ነው ያሉት ተብሏል፡፡

እናም አሁን ትራምፕ ግሪንላንድን ለመያዝ የአሜሪካን ጦር ይጠቀሙ ይሆን ወይ ተብሎ እየተነሳ ሲሆን፤ትራምፕ ግን ምን ሊወስኑ እንደሚችል ከእሳቸው ውጪ ሊያውቅ የሚችል እንደሌለ ይነሳል፡፡

አውሮፓ በግሪንላንድ ላይ ትኩረታቸውን ከማድረግ ይልቅ በዩክሬኑ ጦርነት ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባቸው ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን ብዙዎች አሁንም ቢሆን ወታደራዊ አማራጩ ከጠረጼዛው ላይ እንዳለ ነው የሚያምኑት፡፡ ከዚህ በተጫማሪ ትራምፕ ይህንን የአሜሪካን አካሄድ የማይደግፉ 8 የአውሮፓ ሀገራት ላይ የንግድ ታሪፍ እንደሚጥሉ መግለጻቸው አይዘነጋም፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe