ሁለተኛ ወሩን የያዘው የአሜሪካ፡እስራኤል እና ኢራን ጦርነት የጦርነቱን ግቦች በማሳካት ወደ መጠናቀቁ እየተቃረበ መሆኑን ትራምፕ ገልጸዋል፡፡ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራኑ ጦርነት መቼ እንደሚያበቃ ቀን ቆርጠው ተናግረዋል፡፡
ትራምፕ በሁለት አልያም በሦስት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ የጦርነቱ ፍጻሜ ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል፡፡ የካቲት 21 ጦርነቱ ሲጀመር ፕሬዝዳንት ትራም ከአራት እስከ አምስት ሳምንት ባለው ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ማለታቸው ይታወሳል፡፡ አሁን ደግሞ ተጨማሪ ሁለት እና ሦስት ሳምንታትን እንደሚፈጅ ገልጸዋል፡፡ ትራምፕ አክለውም ዋሽንግተን ጦርነቱን ለማስቆም ከቴህራን ጋር ወደ ስምምነት መምጣት አይጠበቅባትም ብለዋል፡፡
ጦርነቱ የሚቆመመው የኢራን የኒውክሌር አቅም እንዳይመለስ ሆኖ ሲዳከም ብቻ መሆኑን በመግለጽ፡፡ ማርክ ሩቢዮም የኢራኑ ጦርነት ፍጻሜ እቀረበ ነው ነገር ግን ነገ፤አልያም ከነገ ወዲያ ብለን መናገር ግን አንችልም ብለዋል፡፡ በተመሳሳይ ፕሬዝዳንት መሱድ ፔዜሽኪያን ኢራን ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር ያለውን ጦርነት ለመቋጨት ዝግጁ መሆኗን ገልጸው ነገር ግን ኢራን ዳግም ጦርነቱ እንዳይቀሰቀስ ዋስትናን ትፈልጋለች ብለዋል፡፡
ከዋይት ሐውስ በኩል እየወጡ ያሉ መረጃዎች ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ላይ የምታደርውን ወታደራዊ ዘመቻ በጣም በቅርቡ እንደምታቆም የሚያመላክት ሆኗል፡፡//

