ፕሬዝዳንቱ ለአሜሪካ የላኩት ምክረ ሃሳብ ዝርዝር ጉዳይ የተባለ ነገር የለም፡፡
ሩሲያ እና ዩክሬን የአሜሪካ ተወካይ አደራዳሪዎች እስቲቭ ዊትኮቭ እና ጃሬድ ኩሽነር ጉብኝት እንደሚያደርጉ በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡ ዊትኮቭ እና ኩሽነር ባለፈው ጥር ወር ላይ ወደ ሞስኮ ተጉዘው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ወደ ኪቭ ግን እስካሁን አልተጓዙም፡፡
ፕሬዝዳንቱ ሀገራቸው የሩሲያውን ጦርነት ለማስቆም ምክረ ሃሳብ ልከናል ያሉት ጦርነቱን በ24 ስዓት እንዲሚያጠናቅቁት ቃል ገብተው ለነበሩት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ነው፡፡
የሩሲያ ዩክሬኑ ጦርነት ምንም አይነት መፍትሔ ሳይሰጠው አራት ዓመት ከመንፈቅ አልፎታል፡፡ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ከሰሞኑ አሜሪካን ጨምሮ ሌሎች የምዕራብ ሀገራት ወዳጆቻው የዩክሬንን የአየር መከላከያ ስርዓት እንዲያጠንክሩ ጥሪ እያቀረቡ ባሉበት ወቅት ነው ይህንን ያሰሙት፡፡
እንደ ዘለንስኪ እምነት አሜሪካ ለዩክሬን የአየር መከላከያ ስርዓት የምትሰጥ ከሆነ እንዲሁም በሞስኮ ላይ ጫናዎችን የምታሳድር ከሆነ ሩሲያ ጦርነቱን የማራዘም እቅዷን በመተው ወደ ንግግር ጠረጼዛው ትዞራለች የሚል ነው፡፡
አሜሪካ የዩክሬኑ ጦርነት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲፈታ ለማድረግ በሚል በዚህ ዓመት ሦስት ጊዜ ንግግሮች እንዲደረጉ ማድረጓ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ይህ የአሜሪካ ጥረት በመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት ምክንያት ሊገፋበት አልተቻለም፡፡
በየካቲት 21 አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር ወደ ቀጥተኛ ጦርነት በመግባታቸው የዩክሬኑን ጦርነት አባገና የሚለው ሳይገኝ ቀጥሏል፡፡ በዚህ መሃልም ሞስኮና ኪቭ እጅግ ከባድ የተባሉ ጥቃቶችን በማድረስ ቀጥለዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ከሰሞኑ ሩሲያ ወደ 50ሺ የሚደርሱ ወታደሮችን ወደ ጦር ግንባር የማሰማራት እቅድ እንዳላት መናገራቸው አይዘነጋም፡፡ ምንም እንኳን ሞስኮ ይህንን የፕሬዝዳንቱን ውንጀላ አትቀበለውም፡፡//

