ፕሬዝዳንት ፑቲን አውሮፓ ጦርነቱን የሚፈልገው ከሆነ ሩሲያ ለዚያ ዝግጁ ነች ሲሉ ዛቱ

ፕሬዝዳንት ፑቲን ከባድ የጦርነት ማስጠንቀቂያ ሰጡ፡፡ አውሮፓ ጦርነቱን የሚፈልገው ከሆነ ሩሲያ ለዚያ ዝግጁ ነች ሲሉ ዝተዋል፡፡

የሩሲያውፕሬዝዳንት ፑቲን አውሮፓ ምርጫውን ጦርነት የሚያደርግ ከሆነ ሩሲያ ለዚህ ዝግጁ ነች ሲሉ አስጠነቀቁ፡፡

ፑቲን የአውሮፓ መሪዎች በፕሬዝዳንት ትራምፕ የሚመራውን የሰላም እቅድ እያደናቀፉ ነው ብለዋል፡፡ አሜሪካ የዩክሬኑ ጦርነት እንዲቋጭ ጥረት ብታደርግም በአውሮፓ መሪዎች ምክንያት እንቅፋት እየገጠመው ነው ሲሉ መሪዎችን ወቅሰዋል፡፡ በተጨማሪም አብዛኞቹ የአውሮፓ ሀገራት ለዩክሬኑ ጦርነት የሚያቀርቡት የሰላም እቅድ በፍጹም በእኛ በኩል ተቀባይነት የሌለው ነው ብለዋል፡፡

ፑቲን ትላንት ማክሰኞ ነው ሞስኮ ከአውሮፓ ሀይሎች ጋር ወደ ጦርነት መግባት እንደማትፈልግና አስፈላጊ ከሆነ ግን ዝግጁ እንደሆነች የተናገሩት፡፡እኛ በፍጹም ከአውሮፓ ጋር ጦርነት ውስጥ መግባት ፍላጎ የለንም፤ነገር ግን በእነሱ በኩል ይፋ ምርጫ ካለ እኛ አሁንም ዝግጁ ነን ማለታቸውን RT አስነብቧል፡፡

ፑቲን ይህንን ንግግር ያሰሙት ወሳኝ የተባለው የአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮቭ እና ኩሽነር በሞስኮ ተገኝተው የሚያደርጉት ውይይት እየተጠበቀ ባለበት ስዓት ነበር፡፡
ፕሬዝዳንት ፑቲን ሩሲያ  አውሮፓን የማጥቃት ምንም አይነት እቅድ እንደሌላት አንስተዋል፡፡ ነገር ግን ለዚህ የሚገፉ ድርጊቶች በአውሮፓ የሚደረጉ ከሆነ ሩሲያ ለጦርነቱ ዝግጁ ናት ብለዋል፡፡

አሁን ዓለም ሞስኮ ከአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛ ጋር የተደረገው ውይይት የዩክሬኑን የጦርነት ሁኔታ ይለውጠው ይሆን ወይ በሚል እየጠበቀው ይገኛል፡፡

ወይ ደግሞ የአዲስ ጦርነት ጅማሮ ማለትም ከአውሮፓ ጋር ወደ ጦርነት የሚገባበትን እድል ሊፈጥርም ይችላል በየሚል አስተያየትም ሲሰጥበት ቆይቷል፡፡

ክሪሚሊን ፑቲን ከአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮቭ እና የፕሬዝዳንቱ አማካሪ ኩሽነር ጋር የተደረገው ውይይት መጠናቀቁንና ገንቢ እንደነበር አስታውቋል፡፡ ፑቲን ለአስምት ስዓታት ያህል ነው ከአሜሪካውል ልዩ መልዕክተኛ እና ከትራምፕ አማካሪው ኩሽነር ጋር ያደረጉት፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወደ ዋይት ሐውስ እንደተመለሱ በ24 ስዓታት ውስጥ የዩክሬኑን ጦርነት እንደሚቋጩት ቃል ገብተው ነበር፡፡ ነገር ግን እስካሁን ይህ ነው የሚባል ተጨባጭ ውጤት ማምጣት አልቻሉም፡፡

ቢሆንም ግን ቃላቸው እውነት ሆኖ እንዲታይ የተለያዩ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን ከማድረግ ግን አልታቀቡም፡፡

ይህ አሁን የቀረበው ባለ 28 ነጥቡ እቅድ በአውሮፓ መሪዎች ዘንድ እና በዩክሬን ባለስልጣናት በኩል ለሩሲያ ፍላጎት ያደላ ነው በሚል ትችት ቀርቦበታል፡፡

ሩሲያ ለድርድር አላቀርባቸውም ከምትልባቸውና በአውሮፓ ሀገራት በኩል ደግሞ ምን ሲሆን ከተባሉት ጉዳዮች መካከል ውስጥ ዩክሬን በፍጹም የኔቶ አባል እንዳትሆን የሚለው፤ሩሲያ ይዛቸው ለምትገኛቸው ለክሪሚያ፡ዶንባስ፡ዣፖሮዣ እና ለኬርሶን እንደ ሩሲያ ግዛት ሆነው እውቅና እንዲሰጣቸው የሚሉት ይገኙበታል፡፡/

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe