ፕሬዝዳንት ፑቲን የዩክሬንን ዋና መዲናን የማዳን እቅድ የለንም አሉ

ፑቲን አራት የዩክሬን ግዛቶችን የመቆጣጠር እቅዳቸውን ሩሲያ እንደምትገፋበትም አሳውቀዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ፑቲን ሩሲያ አራት የዩክሬን ግዛቶችን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር የምታደርገውን ግፊት የምትቀጥል ሲሆን፤ከ4 ዓመታት በላይ ባስቆጠረው ጦርነት ውስጥ ግጭቶችን ለመቀነስ ዩክሬን አቅርበዋለች ያሉትን ሀሳብ ውድቅ አድርገዋል፡፡

ዩክሬን የሁኔታዎችን መባባስ ለመቀነስ እንደ አንድ እርምጃ የጋራ የረጀም ርቀት ጥቃቶችን የማቆም ሀሳብ አቅርባ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ ሀሳቡ የቀረበው ወደ ዩክሬን ግዛት የሚሰነዘሩት የአጸፋ ጥቃቶች እጅግ ጠንካራ እና አጥፊ በመሆናቸው ነው ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ፑቲን የተኩስ አቁም ፋታ መስጠት ዩክሬን እንደገና እንድትደራጅ እድል መስጠት ነው፤እኛ ደግሞ የኪቭን አገዛዝ ማዳን የእቅዳችን አካል አይደልም ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ አሜሪካ ከኢራን ጋር ያላትን ውጥረት ካጠናቀቀች በኋላ፤ሀገራቸው ከዋሽንግተን ጋር የዩክሬኑን ጦርነት ለማጠናቀቅ የምታደርገውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ተቀጥላለች ብለዋል፡፡

በቅርቡ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ከአቻቸው ፑቲን ጋር ፊት ለፊት ለመገናኘት ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፤ፑቲን ጥያቄያቸውን ውድቅ ማድረጋቸውም ይታወቃል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe