ሃይኒከን ኢትዮጵያ “ጠጥቶ ያለመንዳት” ዘመቻ በአዲስ አበባ አስጀመረ

ሃይኒከን ኢትዮጵያ ከአዲስ ሜትር ታክሲ ጋር በመተባበር “በልክ በአግባብ በሀላፊነት – አራዳ ከጠጣ የማይነዳ” በሚል መሪ ቃል መጠጥን ከማሽከርከር ጋር ተያይዞ የሚያስከትለውን አደጋ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ዘመቻ በይፋ አስጀመረ።
‘ ዘመቻው 50 የአዲስ ሜትር ታክሲዎች ላይ በሚለጠፍ መልዕክቶች ለስድስት ወራት የሚቆይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ይሰጣል።
ሃይንከን ኢትዮጽያ አልኮል ጠጥቶ ማሽከርከር የሚያደርሰውን አደጋ በመገንዘብ መልዕክቱ በተመረጡ የሜትር ታክሲዎች አማካኝነት ሲተላለፍ በቀን ውስጥ ለ2ሚሊዮን ሰዎች ይደርሳል የሚል ግምገማ እንዳለው ተናግሯል።
ለስድስት ወራት በሚቆየው ዘመቻ ደግሞ በአዲስ አበባና ታክሲዎቹ በሚንቀሳቀሱበት የአዲስ አበባ ዙሪያ መልዕክቱ 300 ሚሊዮን ለሚደርሱ ሰዎች ይደርሳል የሚል ግምት እንደተያዘ ተነግሯል።
ሃይንከን ኢትዮጵያ ይህንን ዘመቻ ሲያከናውን ምንም አይነት የአልኮል መጠጥን የሚያበረታታም ይሁን መልዕክቱንም ማን እንዳስተላለፈው የሚገልፅ ምንም አይነት ምልክት ሳይጠቀም እንደሚሆንም ተገልጿል።
ድርጅቱ ጠጥቶ ማሽከርከር የሚያስከትለውን አደጋ በመገንዘብ ሃላፊነት እንደሚሰማው ተቋም ይህንን ማድረግ እንደመረጠ የተቋሙ የሴስቴነብሊቲ የውጭና መንግስታዊ ጉዳዮች ሀላፊ አቶ ፈቃዱ በሻህ በዘመቻ ማስጀመሪያው ላይ ተናግረዋል።

Heineken Ethiopia

በኢትዮጽያ በትራፊክ አደጋ ምክንያት በየዓመቱ ከ4ሺ በላይ ሰዎች ህይዋታቸውን ያጣሉ። ለዚህ ደግሞ አንዱ ምክንያት አልኮል ጠጥቶ በማሽከርከር ነው።
ሃይንከን ኢትዮጵያ ከዚህኛው ዘመቻ ባሻገር እድሜያቸው ከ21 ዓመት በታች ያሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አልኮል አልቀምስም የሚል ስልጠና እየሰጠ እንደሆነ ገልጿል። እስካሁንም በዚህ ስልጠና 11 ዩኒቨርሲቲዎችን መድረስ ተችሏል።
በዚህ ”የበልክ” ዘመቻ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ የሃይንከን ኢትዮጽያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ባርት ዲ ኬኒንክንን ጨምሮ የአዲስ ሜትር ታክሲ ዋና ስራ አስኪያጅና ከአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ተወክለው የተገኙ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በትላንትናው እለት ዘመቻው በይፋ ተጀምሯል።//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe