ሃይንከን ኢትዮጵያ ሁለት አርቲስቶችን አምባሳደር አድርጎ ሾመ

ሃይንከን ኢትዮጵያ ለማህበራዊ አገልግሎት ሥራዎቹ አርቲስት ሸዊት ከበደ እና አርቲስት ይገረም ደጀኔ አምባሳደሮቹ አድርጎ በዛሬው እለት መምረጡን ይፋ አደረገ።
ሃይንከን ኢትዮጵያ ለችግረኛ ወገኖች ደረጃዉን የጠበቀ መኖሪያ ቤት ገንብቶ ማስረከብ፣ ለሥራ – አጥ ወገኖች የስራ ዕድል በመፍጠር እና የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን ማከናወኑን እየቀጠለ ይገኛል፡፡
ሁለቱ አርቲስቶቻችን በአዘጋጅነትና በተዋናይነት በሚሳተፉበት ” የሚሰቶቼ ባሎች ” የተሰኘው ቲያትር በዛሬው እለት በዓለም ሲኒማ በተመረቀበት ወቅት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በአምባሳደርነት የተመረጡት ሁለቱ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎቹ ከየትኛዉም የሃይንከን ኢትዮጵያ ምርቶች ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸውና ማኅበራዊ ሥራዎቹ ላይ ብቻ በማተኮር የሚሰሩ ናቸው ተብሏል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe