ሃይንከን ኢትዮጵያ በጉለሌ እና በአቃቂ ክፍለ ከተሞች 22 ሺ ችግኞችን የመትከል መርሐ ግብር አከናወነ

ሃይንከን ኢትዮጵያ ከጉለሌ እና አቃቂ ክፍለ ከተሞች አስተዳደሮች ጋር በመተባበር በእንጦጦ ተራራ እና በአቃቂ ቃሊቲ (ቂሊንጦ ወረዳ ዘጠኝ አካባቢ)  22 ሺ ችግኞችን የመትከል መርሐግብር አከናውኗል።
የሃይንከን ኢትዮጵያ የሰስተይኔቢሊቲ የውጭ እና የመንግስት ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ፍቃዱ በሻህ እንደገለጹት ይኸንን ተግባር ላለፉት ተከታታይ ዓመታት ድርጅቱ ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸው የዚህ ፕሮጀክት ዋና ዓላማም በዝናብ ምክኒያት የሚፈጠር የውሃ ፍሰት (Runoffs) ተቆጣጥሮ ለማስተካከል እና ምርት በማምረት ሂደት ላይ ጥቅም ላይ የዋለውን ውሃ ለመተካት ያለመ ነው ።
መርሐግብሩም የሃይንከን ኢትዮጵያ የማኀበራዊ በጎ ተፅዕኖ አምባሳደሮች፣ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እና የሃይንከን ኢትዮጵያ በጎ ፈቃደኛ ሰራተኞች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከናውኗል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe