ሃይንከን ኢትዮጵያ የእናቶች የሥራ እድል ፈጠራ ፕሮጀክት አስመረቀ

ሃይንከን ኢትዮጵያ ማኀበራዊ ኃላፊነቱን ከሚወጣባቸው ፕሮጀክቶች አንዱ የኾነውን የእናቶች የሥራ እድል ፈጠራ ፕሮጀክት አስመረቀ።
ሃይንከን ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት ሥራ ያስጀመራቸው በቂሊንጦ አካባቢ በዶሮ እርባታ ሥራ የተሰማሩ 30 ያኸል እናቶችን ነው።
ፕሮጀክቱ በአራት የተለያዩ የሃገራችን አካባቢዎች ከተሞች ማለትም በአዲስ አበባ፣ ሃረር፣ በደሌ እና ባህርዳር ለሚገኙ ወገኖች ተገቢውን ስልጠና በመስጠት ወደ ሥራ በማስገባት ላይ ይገኛል።
ስድስት ሚልየን ብር በጀት የተያዘለት ይኸው ፕሮጀክት በአጠቃላይ ለ120 ወገኖች የሥራ ዕድል ይፈጥራል።
ሃይንከን በዚህ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፕሮጀክቱ ከዚህ ቀደም በሃረር በሳሙና ማምረት እንዲሁም በበደሌ ደግሞ በከብት እርባታ 60 ወጣቶችን ወደ ሥራ ማስገባት ችሏል።
SourceDere Tube

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe