ህንድ በየሦስት ደቂቃው አንድ ሰው በመኪና አደጋ ህይወቱን የሚያጣባት የዓለማችን ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ የሚደርስባት ሀገር ነች ተባለ፡፡
በ2023 ብቻ በመንገድ ላይ በተሸከርካሪዎች አማካኝነት ባጋጠሙ አደጋዎች ከ172ሺ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸውን አዲስ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡ ይህም ማለት በአማካኝ በየቀኑ 474 ሰዎች እንዲሁም በየሦስት ደቂቃው ደግሞ አንድ ሰው ለሞት ተዳርጓል ማለት ነው፡፡
በህንድ በ2023 ከ480ሺ በላይ የተሸከርካሪ አደጋ የተመዘገበ ሲሆን በዚህ ሳቢያም ከ170ሺ በላይ ሰዎች ለሞት እንዲሁም መቶሺዎች ደግሞ ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል ነው የተባለው፡፡
ከሟቾቹ ውስጥ 10ሺ ያህሉ ህጻናት ናቸው፡፡ ሪፖርቱ እንዳለው ከልክ በላይ መፍጠን ወነኛው መንስኤ ነው ያለ ሲሆን፤በብስክሌት እና ሞተር ሳይክል ላይ በሚደርሱ አደጋዎች ሄልሜት ባለማድረግ 54ሺ ሰዎች እንዲሁም 16ሺ የሚሆኑት ደግሞ የመቀመጫ ቀበቶ ባለማሰር ለሞት ተዳርገዋል፡፡
ሌላው መንስኤ ደግሞ ከልክ በላይ ሰዎችን መጫን እንደሆነ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡/

