ህወሃት የባድ መሣሪያ ትጥቅ የሚፈታው የውጭ ኃይሎች ያሏቸው ሲወጡ እንደሆነ አስታወቀ

በኢትዮጵያ መንግሥትና በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ(ህወሓት) መካከል የተፈረመው የሰላም ስምምነት በተግባር በመተርጎም ላይ ነው ሲሉ የትግራይ ኃይሎች ዋና አዛዥ ጀነራል ታደሰ ወረደ አስታወቁ።

ጀነራል ታደሰ ትናንት በትግራይ ቴሌቪዥን በሰጡት ማብራሪያ በአሁኑ ጊዜ ተኩስ መቆሙን ገልጸው፣ፕሪቶሪያ ደቡብ አፍሪቃ ላይ ስለተደረሰው የሰላም ስምምነት የትግራይ ኃይሎችን ማስረዳትና ከውጊያ ቀጣናም የማራቅ ስራ መቀጠሉን መናገራቸውን የመቀሌው DW ወኪል ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ ዘግቧል። ጀነራሉ በገለጻቸው ከዚህ በኋላ የውጊያ ግንባሮችን ማፍረስና ሰራዊቱንም ወደተቀመጠለት ስፍራ መውሰድ ይቀጥላል ብለዋል። የሰላም ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ ለመተግበር በትግራይ በኩል ዝግጁነት እንዳለ የጠቆሙት ጀነራሉ ሆኖም ትጥቅ ማስፈታቱ የትግራይን ህዝብ ደኅንነት ባስጠበቀ መልኩ እንደሚተገበር፤ ከባድ መሣሪያ ማስፈታትም የውጭ ኃይሎች ያሏቸው ሲወጡ እንደሚከናወን ተናግረዋል።

ጀነራል ታደሰ በማብራሪያቸው በሁለቱ ወገኖች ሠራዊት አዛዦች በኩል መግባባት መፈጠሩን አስታውሰው በአሁኑ ጊዜ ደግሞ በአንዳንድ አካባቢዎች የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና «የትግራይ ኃይሎች» ሲሉ የገለጿቸው በአካል ጭምር መገናኘት መጀመራቸውንም እንደተናገሩ ሚሊዮን ዘግቧል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe