ህገወጥ ንግድ ብሄራዊ ባንክ የሚገባውን ወርቅን ለማስረከብ ፈተና ሆኗል!

በሀገር ውስጥ ያለዉ ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ወደ ብሄራዊ ባንክ የሚገባዉን ወርቅ ለማስረከብ ፈተና ሆኖብኛል ሲል የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል ገልጿል፡፡ለመንግስት ገቢ የሚሆነዉን ገንዘብ በመሰብሰብ ሂደት ላይ የክልሉ ፈተና ምንድን ነዉ ሲል አሃዱ የክልሉን ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ሕይወት አሰግድን ጠይቋል፡፡

በኢትዮጵያ ስር እየሰደደ የመጣዉ ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ በክልሉ ያሉትን ማእድናት እና ሌሎችም ሃብቶች በህጋዊ መንገድ ለመጠቀም ተቸግረናል ነዉ ያሉት ሃላፊዋ፡፡በተለይም በክልሉ ያለዉ እና ወጥቶ ለብሄራዊ ባንክ መግባት ያለበትን የወርቅ ማእድን ለማስገባት ያለዉ ፈተና ከፍተኛ ነዉ ለምን ከተባለ ደግሞ ህገወጥ ነጋዴዎች አግባብ ባለሆነ መልኩ እየሸጡት እንደሆነ ነው ያብራሩት፡፡

ክልሉ ገና እንደ አዲስ እየተቋቋመ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከዚህ በፊት ተሰርተዉ ማለቅ የነበረባቸዉ እንደ የክፍያ ማሽን ማዘመን ስራዎች አለመጠናቀቃቸዉ ሌላኛዉ ማነቆ መሆኑም ተነስቷል፡፡ በተጨማሪም ከሃሰተኛ ደረሰኝ እና ከዋጋ በታች በሚቆረጡ የደረሰኝ ወንጀሎች ላይ ሲሳተፉ የተገኙ 6 ግለሰቦችም በህግ ተጠያቂ መደረጋቸዉን ነው የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል የገለጸው፡፡

[Ahadu]

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe