ለነባሩ የአማራ ክልል ሰንደቅ ዓላማ ማሻሻያ ሶስት አማራጮች ቀረቡ

ነባሩን የአማራ ክልል ሰንደቅ ዓላማ ለማሻሻል በክልሉ ም/ቤት ከ4 ወራት በተላለፈው ውሳኔ መሰረት፣በአማራ ክልል ርዕሰ-መስተዳደር አገኘሁ ተሻገር ተሰይሞ ወደ ስራ ገባው የባለሞያዎች ቡድን ሲያካሂድ የቆየውን ጥናት አጠናቋል፡፡

ይህንኑ ተከትሎም፣የአማራ ብሄራዊ ክልል ምክር ቤት የሰንደቅ ዓላማ አጥኝ ኮሚቴ ክልሉን ይወክላሉ ባለቸው የሰንደቅ ዓላማ አማራጮች ዙሪያ የህዝብ አስተያየት ለማሰባሰብ፣ከሀይማኖት መሪዎች፣ከከሀገር ሽማግሌዎች፣ከተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ከምሁራን፣ከክልሉ የመንግስት አመራሮች እና ከሲቪል ማህበራት ተወካዮች ጋር ዛሬ ውይይት አካሄዷል፡፡

በዚሁ መሰረት፣የአማራን ህዝብና እሴት የሚያንጸባርቁ፣በርካታ አስተያየቶች የተካተቱባቸው እና ከአለም አቀፍ የሰንደቅ ዓላማ መርሆዎች አንፃር የተቃኙ ናቸው የተባሉ ሶስት የማሻሻያ ሃሳቦች በስዕል ተደግፈው ቀርበዋል::

ከተሳታፊዎች ወገን በቀረቡት አማራጮች ላይ በተሰጡ አስተያየቶች የአንበሳ ምስል ቢጨመር፣የክልሉ አሁናዊ ካርታ ቢቀመጥ፣የጋሻ እና የጦር ምስል ቢካተት፣የመስህብ ሃብቶች ቢወከሉ የሚሉና ሌሎች አስተያየቶችን ተሰጥተዋል፡፡

አጥኝ ቡድኑም ከህዝብ የተሰጡ አስተያየቶችን አሰባስቦ በግብዓትነት በመጠቀም የመጨረሻዎቹን የሰንደቅ ዓላማ የማሻሻያ አማራጮች ለአማራ ክልል ም/ቤት እንደሚያቀርብ ብስራት ሬዲዮ ከክልሉ ም/ቤት ባገኘው መረጃ ተረድቷል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe