ለንግድ ወደ ሀገር የሚገቡ እቃዎች የሚባሉት የትኞቹ ናቸው ?

ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት በስተቀር ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ማናቸውም ዕቃዎች ለንግድ የሚውሉ ዕቃዎች ናቸው።

1. በፌደራል እና በክልል የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ መሰረት ለመንግስት መ/ቤት በተሰጠው ትርጉም ውስጥ የተካተቱ የፌደራል መንግስት መ/ቤቶች እና የክልል መንግስታት መ/ቤቶች የሚያስገቧቸው ዕቃዎች፣

2. ለትርፍ ያልተቋቋሙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ማህበራት የሚያስገቧቸው እቃዎች (ከተቋቋሙበት አላማ ውጭ በንግድ መልክ የሚያስገቧቸውን ዕቃዎች አይጨምርም)፣

3. በዲፕሎማቲክ እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሰረት ከንግድ ትርፍ ግብር ነፃ የሆኑ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ የውጭ ዲፕሎማቲክ ወይም ኮንሱላር ሚሲዮኖችና የእነዚሁ አባላት የሚስገቧቸው ዕቃዎች፡፡

4. የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ ቁጥር 51/2010 መሰረት የግል መገልገያ እቃዎችን ከቀረጥ ነፃ ወይም ቀረጥና ታክስ ከፍለው እንዲያስገቡ የተፈቀደላቸው ግለሰቦች የሚያስገቧቸው እቃዎች፣

5. በጉምሩክ ታሪፍ ደንብ 2ኛ መደብ (ለ) ተጠቃሚ ሆነው እቃዎችን የሚያስገቡ ግለሰቦችና ድርጅቶች፣

6. በፌደራልና በክልል ኢንቨስትመንት ባለስልጣን ከገቢ ግብር ነፃ የመሆን መብት የተፈቀደላቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች በእፎይታው ጊዜ ውስጥ የሚያስገቧቸው እቃዎች፣

7. የአምራችነት ፍቃድ ያላቸው ሰዎች ወይም ድርጅቶች ለሚያመርቷቸው ዕቃዎች በግብዓትነት የሚጠቀሙባቸው ጥሬ ዕቃዎች እና ለካፒታል ዕቃዎች የሚያገለግሉ መለዋወጫዎች ፣

8. ኢንዱስትሪዎችን ለማቋቋም ወይም ለማስፋፋት ወይም ለሃይል ማመንጨት ወይም የመገናኛ አገልግሎት ለመዘርጋት ወዘተ ወደ አገር የሚገቡ የካፒታል ዕቃዎች ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ወይም ጉዳዩ ከሚመለከተው አካል የካፒታል ዕቃዎች መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከቀረበ፣

9. የንግድ ትርኢት ለመሳተፍ የሚመጡ የውጪ አገር ድርጅቶች ምርታቸውን ለማስተዋወቅ ወደ ውስጥ ይዘውት የሚገቡት እቃዎች፣

10. በማዕድን እንዲሁም በፔትሮሊየም ስራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ለነዚህ ስራዎች አገልግሎት እንዲሰጡ የማያስገቧቸው እቃዎች እና

11. ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውሉ እቃዎች

ከላይ ከተዘረዘሩት ውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ሌሎች ማናቸውም እቃዎች ለንግድ የሚውሉ ዕቃዎች ተብለው ይታያሉ፡፡

ወደ አገር ከሚገቡ ለንግድ ከሚውሉ ዕቃዎች የቅድሚያ ግብር ስለመሰብሰብ ፦

1. ዕቃዎቹ ወደ አገር በሚገቡበት ጊዜ በቅድሚያ ግብር የሚከፈለው በጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤቶች በኩል ይሆናል ፡፡

2. በጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤቶች ለንግድ ከሚውሉ እቃዎች የቅድሚያ ግብር ሲሰበስቡ የግብር ከፋዩን ሥም፤ አድርሻ እና የግብር ከፋዩን መለያ ቁጥር በመጠቀም መመዝገብና ሂሰቡን በዚሁ መሠረት መያዝ አለባቸው።

3. በጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤቶች ከተከፋይ ሂሣቦች ላይ በቅድሚያ ተቀናሽ የሚደረገው የቅድመ-ታክስ ክፍያ ገቢ ባለቤት ለሆኑት ገቢ ሰብሳቢ አካላት በተዘረጋው ሥርዓት መሠረት ይተላለፋል፡፡

ምንጭ፦ የገቢዎች ሚኒስቴር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe