ለአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ የኮማንደርነት ማዕረግ ተሰጣት!

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ለአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ልዩ የኒሻን ሽልማት እና የኮማንደርነት ማዕረግ አበርክቶላታል፡፡

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በተሰማሩበት የሥራ መስክ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ 78 የኮሚሽኑ ስፖርት ክለብ አባላት የማዕረግ፣ የገንዘብና የልዩ ኒሻን ሽልማት አበርክቷል፡፡

በሽልማት ፕሮጋራሙ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ልዩ የኒሻን ሽልማት የተበረከተላት ሲሆን በኮሚሽኑ የኮማንደርነት ማዕረግም ተሰጥቷታል፡፡

ኮማንደር አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በተሰጣት ሽልማት መደሰቷን ገልጻ በማረሚያ ቤት ስፖርት ክለብ ትንሽ ልጅ ሆና በመቀጠር አሁን ለደረሰችበት ደረጃ መብቃቷንም አንስታለች፡፡

ሽልማቱ የማረሚያ ስፖርት ክለብ ወጣት አትሌቶች ጠንክረው እንዲሰሩ፣ እንዲበረታቱና የተሻለ ደረጃ እንዲደርሱ ያደርጋል ያለችው አትሌቷ በተለያዩ የውድድር መስኮች የኮሚሽኑ አትሌቶች ውጤታማ መሆናቸውን ገልፃለች፡፡

ኮሚሽኑ ለ34 ስፖርተኞች ከረዳት ሳጅን እስከ ኮማንደር ድረስ የማዕረግ ዕድገት ሲሰጥ ለ19 ስፖርተኞች ደግሞ የገንዘብ እና ለ13 ስፖርተኞች የእርከን ጭማሪና የገንዘብ ሽልማት ሰጥቷል፡፡

ለአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ የተበረከተው ልዩ የሜዳሊያ ሽልማት ከረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ቀጥሎ ለ2ኛ ጊዜ መሆኑን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe