ይህች እናት ብራዚላዊት ስትሆን ወ/ሮ ሲሊቪያ ግሬኮ ትባላለች።
ይሄ ልጇ አይነስውር ቢሆንም እግር ኳስ መከታተል ይወዳል። የልጇን የኳስ ፍቅር ያየችውና የሁልጊዜም ደስታውን ማየት የምትሻው እናትም በየስታዲዮሙ አብራው እየሄደች የጨዋታውን እንቅስቃሴ የመመልከትን ያክል ግልፅ በሆነ ሁኔታ ትዘግብለታለች።
ይሄ ለልጇ ደስታ ብላ የጀመረችው የኮሜንታተርነት ስራ በሌሎች ጆሮ ገባና ሞቅ ያለ እንጀራ እና እውቅና ይዞላት መጥቷል።
የፊፋ የምርጥ ደጋፊ ሽልማት ከብዙ ጥቅማጥቅም ጋር ተሰጥቷታል።
በብራዚል የሚገኝ የእግር ኳስ ጨዋታን በቀጥታ ስርጭት የሚያስተላልፍ ሬድዮ ጣቢያም ኮሜንታተር አድርጎ ዳጎስ ባለ ደመወዝ እንደቀጠራትና በድንገት ከዝቅተኛ ነዋሪነት ወደ ታዋቂ ኮሜንታተርነትና ባለከፍተኛ ገቢነት መሸጋገሯ ተሰምቷል::
ለአይነስውር ልጇ ኮሜንታተር የሆነች እናት

