ለወራት በሆርሙዝ ሰርጥ ተይዛ የነበረችው “MV ጊቤ” የኢትዮጵያ መርከብ ተለቀቀች

ለወራት በሆርሙዝ ሰርጥ ተይዛ የነበረችው “MV ጊቤ” ወደ ጅቡቲ እየተመለሰች ነው
በሆርሙዝ ሰርጥ ለወራት ተይዛ የነበረችው የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መርከብ “MV ጊቤ” በሰላም ወደ አገር ቤት እየተመለሰች መሆኑ ተገለጸ።
በአሜሪካ፣ በእስራኤል እና በኢራን መካከል ተፈጥሮ በነበረው አለመግባባት ምክንያት ጉዞዋ ተስተጓጉሎ የቆየው መርከቧ፣ በአሁኑ ወቅት ከጭነቷ ጋር ወደ ጅቡቲ ወደብ በመጓዝ ላይ መሆኗ ታውቋል።
የኢትዮጵያ ምልክት የሆነችው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሀገሪቱን ሰንደቅ ዓላማ ከሚያውለበልቡ መርከቦች አንዷ የሆነችው MV ጊቤ፣ በአሁኑ ወቅት በኦማን ገልፍ አካባቢ የምትገኝ ሲሆን፣ የፊታችን ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ላይ ወደ ጅቡቲ ወደብ እንደምትደርስ ይጠበቃል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe