ለጥያቄያችን በቂ ምላሽ ስላላገኘን ትግላችንን እንቀጥላለን – የህክምና ተማሪዎች ማኅበር

ጤና ሚኒስቴር ለተለማማጅ የህክምና ተመራቂ ተማሪዎች ጥያቄ አሁንም በቂ ምላሽ አለመስጠቱን የህክምና ተማሪዎች ማኅበር ይፋ አደረገ፡፡ ጤና ሚኒስቴር በተለይ በተለማማጅ የህክምና ተመራቂ ተማሪዎች ቀዳሚ ተነሳሽነት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ፈጣን ርምጃ መውሰዱ እና፤ የሞያ ፈቃድ ለመውሰድ ይጠየቅ የነበረውን ከ450 ሽህ ብር በላይ እንዲቀር መወሰኑ የሚያስመሰግነው ነው ብሏል ማኅበሩ። ኾኖም አሁንም ያልተመለሱት ጥያቄዎች አሉ ብሏል፡፡ የህክምና ተማሪዎች ማኅበር የጤናው ዘርፍ ጉዳዩ ሰሞነኛ ነገር ሆኖ እንዳይቀር ትግላችንን እንቀጥላለን ብሏልም።

ማህበሩ የችግሮች ሁሉ መነሻ የሆነው ወቅቱን የማያማክለው የጤና ስርአት እንዲሻሻልና ጥያቄዎቻችን ሙሉ በሙሉ እንዲመለሱ ትግላችንን በሰላማዊ ሁኔታ አጠናክረን እንቀጥላለን ብሏል፡፡ ሚኒስቴሩ ነባሩ ፖሊሲ እንዲሻሻል ተወስኖ ውይይቶች መደረጋቸውን ጠቀስ አድርጎ ከማለፍ የዘለለ ዝርዝር ነገር በመግለጫው አላንጸባረቀም፡፡ይልቁንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ፖሊሲው ከ 16 አመታት በፊት ሲረቀቅ መከላከልን መሰረት ማድረጉን እና ተላላፊ በሽታዎችን ትኩረት አድርጎ የነበረ ቢሆንም ፖሊሲው ጤናን ፡ የጤና ሙያተኞችን ፡ ተገልጋዮች ማእከል ያደረገ መሆን እንዳለበት ጠቅሰው ፡ አሁን እንደ ስኳር ፡ ካንሰር ፡ የልብ እና መሰል ችግሮች ገዳይ በመሆናቸው ፖሊሲው የማይሻሻልበት ምክንያት የለም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ጤና ሚኒስቴር በርከት ያሉ ጉዳዮች ከመጭው ወር ጀምሮ እንዲሻሻሉ እና ፡ ተከልክለው የነበሩ ጉዳዮች እንዲነሱ መወሰኑን በመግለጫው አትቷል፡፡የህክምና ተማሪዎች ማህበር ግን ትኩረት አሁንም ለጤናው ዘርፍ ፡ ጉዳዩ ሰሞነኛ ነገር ሄኖ እንዳይቀር ትግላችንን እንቀጥላለን በሚል አቋሙን በግልጽ አስቀምጧል፡፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe