ለጾታዊ ጥቃት የፍትሕ ጥያቄ ሽልማት እና ስጦታ መልስ አይሆንም ተባለ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሴቶች ላይ የሚደርስን አካላዊ እና ጾታዊ ጥቃት መኖሪያ ቤት እና ሌሎች ስጦታዎች በመስጠት ሐዘኔታ እና ድጋፍን ማሳየት እየተለመደ መጥቷል ያለው ሴታዊት ጾታዊ ንቅናቄ፤ ድርጊቱ የፍትሕ ስርአቱን የሚያዛባ፣ ጥፋተኞች ተገቢውን ቅጣት እንዳያገኙ የሚያደርግ ነው ብሏል።

የንቅናቄው መስራችና ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ስህን ተፈራ ከአሐዱ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች እና ቤተሰቦቻቸው ስጦታ መስጠት በራሱ ችግር ባይሆንም ለተንዛዛ የፍትሕ ስርአት እየዳረገ እንደሚገኝ ነግረውናል።

“የስጦታዎቹ ትልቅነት ጉዳት ያልደረሰባቸው ሴቶችም ጉዳት እንደደረሰባቸው በማስመሰል እንዲዋሹና እንዲያስመስሉ የማድረግ ዕድሉ ከፍ ያለ ነው” ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት እየተበራከተ ለሚገኘው ፆታዊ ጥቃቶች ተጠያቂው ማን ነው? ማኅበረሰብ ወይስ የሕግ መላላት ሲል ከአሐዱ ለቀረበላቸው ጥያቄም “የሕግ አስተዳዳር ዘርፉ ላይም በርካታ ችግሮች አሉ፡፡ የፀጥታ አካላት ስልጠና ማነስ ጥቃት አድራሾችን እስከ መጨረሻው ተከታትለው ለፍርድ እንዳያቀርቡ እንቅፋት ሆኗል” ብለዋል፡፡

ይህም ደግሞ ከበጀት እጥረት እና በቂ መረጃ ተደራጅቶ ካለመምጣት እርስ በርስ የመካሰስ ሁኔታ ቢኖረውን ይህ የሕግ ክፍትት 30 በመቶውን ቢውስድ ነው ሲሉም አክለዋል።

በኢትዮጵያ ለሚፈጠሩ ፆታዊ ጥቃቶች 70 በመቶውን ኃላፊነት የሚወስደው ማኅበረሰቡ ነው የሚሉት ዶክተር ስህን፤ “ማኅበረሰቡ አጥቂዎችን መሸሸጉ ጥቃቶችን መላመዱ ተደማምሮ አሁን ላለንበት ችግር ዳርጎናል” ብለዋል።

በፊት የሰዎች ሞትም ሆነ ፃታዊ ጥቃቶች አስደንጋጭ ነገሮች እንደነበሩም በማንሳት፤ “ይሁን እንጂ አሁን ላይ ማኅበራዊ ሚድያው ይበልጥ እያጋለጠ ተሰምቶ የማይታወቅ ነገሮች እየተሰማ ነው” ሲሉም ተናግረዋል።

አሁን ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን መስማት ምንም የማያስደነግጥ መሆኑን የሚያነሱት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቿ ሁሉንም ችግር ሕግ መላላት ነው ብሎ መውሰድ ግን አያስችልም ብለዋል።

በኢትዮጵያ ከ4 ሴቶች ውስጥ አንዷ ከ15 ዓመቷ ጀምሮ ጾታዊ ጥቃት እንደሚያጋጥማት በ2016 ዓ.ም የተካሄደው የስነ- ህዝብና ጤና ዳሰሳ ያመላክታል፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe