ለፖፕ ፍራንሲስ የቀብር ሥነ-ርስዓት ወደ ቫቲካን አምርተው አምርተው የነበሩት ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ ወጪ እያባከኑ ነው በሚል ተቋውሞ ገጥሟቸዋል ተብሏል፡፡
ቅዳሜ እለት በነበረው የፖፕ ፍራኒሲስ ቀብር ላይ ለምን ተገኙ በሚል ነው ተቃውሞ የመጣባቸው፡፡
ፕሬዜዳንት ሩቶ ቀብሩ ላይ እንዲገኙ ሌላ ባለስልጣንን መድበው የነበረ ቢሆንም፤በቻይና የነበራቸውን ጉብኝት እንዳጠናቀቁ በድንገት ወደዚያው ማምራታቸውን ተከትሎ አባካኝ በሚል የተወቀሱት፡፡ ፕሬዜዳንቱ በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙ ብቸኛው አፍሪካ መሪም ነበሩ፡፡
ይህን መሠረት አድርገውም ኬኒያውያን ፕሬዜዳንታችን ወጭ ቆጣቢ አይዱም በማለት ድርጊቱን የተቃወሙት፡፡
በርካታ ኬኒያዊያን ከኑሮ ውድነት ጋር እየታገሉ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ፕሬዜዳንቱ ወጭ ቆጣቢ ርምጃዎችን ለመውሰድ ያላቸውን ቁርጠኝነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባ ጉዞ ነበር ብለውታል፡፡
ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ቀብሩን የታደሙት በምክትል ፕሬዜዳንቶች፡ሚኒስትሮች እና የፓርላማ መሪዎች ውክልና ነው፡፡
የቀድሞ ምክትል ፕሬዜዳንት ሪጋቲ ጋቻጓ የፕሬዜዳንቱን ውሳኔ በመተቸት የህዝብን ሃብት አባክኗል ሲሉ ከሰዋቸዋልም ተብሏል፡፡

