ለ10,000 የጤና ባለሙያዎች የመኖሪያ መንደር ሊገነባ ነው

 ሰላም ሄልዚ ኮንሰልታንሲ ፣ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና ጎጆ ብሪጅ ሀውስ በጋራ በመሆን በዛሬው ዕለት ሚያዝያ 10/2014 ዓ/ም በሀገራችን የመጀመሪያውን 10,000 የጤና ባለሙያዎች የመኖሪያ መንደር ለመገንባት የሚያስችል ውጤታም ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱም ላይ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አየለ ተሾመ፣ አቶ አልማው ጋሪ የጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጨምሮ ሌሎች የሥራ አመራር አባላት፣ ሀሳቡን ያመነጨው የሰላም ሄልዝ ኮንሰልታንስ ባለቤት በጄቲቪና በአፍሪ ሄልዝ ቲቪ የጤና ጋዜጠኛው ደረጀ ቱሉ ተገኝተዋል።
ጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በከተማ ውስጥ የሚገኘውን ከፍተኛ የመኖርያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በጥናትና በፈጠራ እውቀት ላይ በመመስረት ሶስት አይነት የግንባታ ሞዴሎችን በመያዝ ወደሥራ መግባቱን አቶ አልማው አስረድተዋል።
በመጀመሪያው ሞዴል እስካሁን 1 ሺ 50 ሰዎችን በ8 ማህበራት በ4 ሳይቶች በማደራጀት በመሀል ከተማ የይዞታ ባለሀብት ግለሰቦችጋር በጋራ ጥቅም በሚደረግ ስምምነት የማልማት ሥራውን ለመጀመር ዝግጅት መደረጉን ጠቅሰዋል።
በመሀል ከተማ ሰፊ ይዞታ ይዘው ማልማት ያልቻሉ ባለይዞታዎች ይዞታቸውን እንዲያጋሩ በማድረግ በጋራ በማልማት ተጠቃሚ ለመሆን በተያዘው እቅድ መሰረት በርካታ ባለይዞታዎች መመዝገባቸውንና ስምምነትም እየተፈፀመ መሆኑን አቶ አልማው ጠቁመዋል።
ጎጆ ብሪጅ በሚቀጥሉት አስር ዓመታት 100ሺ የመኖርያ ቤቶችን ለመገንባት እቅድ ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ ሲሆን በዛሬው እለት በተደረሰው መግባባት መሰረት 10 ሺ የጤና ባለሙያዎች የመኖርያ ቤት ባለቤት እንዲሆኑ እንደሚሰራ አስረድተዋል።
ይህን ድንቅ ሀሳብ ያመነጨው ደግሞ የሰላም ሄልዝ ኮንሰልታንስ ባለቤት እና በጄቲቪና በአፍሪ ሄልዝ ቲቪ የምናውቀው የጤና ጋዜጠኛው ደረጀ ቱሉ ሲሆን የዛሬው ውይይትን ወደመሬት ለማውረድ የብዙ ባለድርሻ አካልት አስተዋጽኦ የሚያስፈልግ መሆኑን ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe