ለ40 ያህል የፌደራል መስሪያ ቤቶች የስም ለውጥ ተደረገ

ዛሬ ይፋ የሆነው የአስፈፃሚ አካላትን መልሶ ስለማደራጀት የሚደነግገውና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀው አዋጅ የተወሰኑ መስሪያ ቤቶችን ላይ የስም ማሻሻያ አድርጓል፡፡ አንዳንዶቹ ቀደም ሲል በእንግሊዝኛ የተሰጣቸውን ስያሜ ወደ  ሀገርኛ ቋንቋ ለመቀየር የተሞከረ ሲሆን ሌሎችን ደግሞ ‹የኢትዮጵያ› የሚል ስም ከፊት ለፊታቸው በመጨመር ሀገራዊ ገጽታን ለማላበስ ተሞክሯል፡፡ ሁሉም በኡጀንሲ ስም ይጠሩ የነበሩት ወደ አገልግሎት ሲቀየሩ በጽሕፈት ቤትነት ይጠሩ የነበሩት ባለስልጣን ሆነዋል፡፡

  • ለምሳሌ ከዚህ በፊት ኮተሜ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ተብሎ ፊደል ላልቆጠረ ብቻ ሳይሆን ለተማረውም ግራ አጋቢ ስም የነበረው የትምህርት ተቋም ዛሬ ‹ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ› ወደሚል ግልፅ ስም ተቀይሯል፡፡
  • ከ50 ዓመታት ላይ በሎተሪ ጨዋታዎች ላይ አተኩሮ ሲሰራ የኖረው ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ስሙን ወደ ‹የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት› ቀይሯል፡፡
  • ግማሽ አማርኛ ግማሽ እንግሊዝኛ ስያሜ ይዞ የቆየው አርቴፌሻል ኢንተለጀንስ ምርምርና ልማት ማዕከል ሙሉ ለሙሉ ስሙን ወደ እንግሊዝኛው ቀይሮ ‹አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስትቲዩት› ተብሏል፡፡
  • ሌላው ባለ እንግሊዝኛ ስያሜው የኢትዮጵያ ባዩቴኖሎጂ ኢንስቲትዩት አልሸሹም ዞር አሉ ስያሜን ይዞ ‹የኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩውት› ተብሏል፡፡
  • የፀረ አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤት ወደ ‹የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን› ተቀይሯል፡፡
  • የኢሚግሬሽን፤ የዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ወሳኝ ኩነትን አስወግዶ ‹የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት› ሆኗል፤
  • ብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት ቲሹን ጨምሮ  ‹ብሔራዊ የደምና ቲሹ ባንክ አገልግሎት› ተብሏል፤
  • ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ሀገር አቀፍንና ኤጀንሲን አስወግዶ ‹የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት› ሆኗል፡፡
  • የስም ማሻሻያ የተደረገላቸው ተቋማት ብዛት 40 ያህል ነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe